በፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር አሳታሚነት የታተመውና በህፃናት ጉልበት ብዝበዛ ላይ ያተኮረው “ታጋቾቹ” የተሰኘ የአጫጭር እውነተኛ ታሪኮች መድበል እንዲሁም ቀደም ሲል ድርጅቱ ካሳተማቸው መጻህፍት ተመርጠው ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎሙት “Blood Price” እና “Ditached in the Jungle” የሚሉ መጻህፍት የፊታችን ሐሙስ በሐርመኒ ሆቴል ይመረቃሉ፡፡
መጻህፍቱ ከወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያና ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በትብብር እንደተዘጋጁ ታውቋል፡፡ በምርቃትሥነ ስርዓቱ ላይ የመንግስት ባለስልጣናት፣የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ የፕሮግራሙ አዘጋጆች አስታውቀዋል፡፡
Monday, 02 March 2015 10:34
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና