Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 21 January 2012 10:58

የፍቅር ጥግ

Written by 
Rate this item
(6 votes)

ይሄን ሁሉ በርካታ ዓመት በፍቅርና በእዳ እንዲሁም በመጠጥ ውስጥ ተዘፍቄ ነበር፡፡

አሌክሳንደር ብሮም

(እንግሊዛዊ ገጣሚ)

ብዙው ወንድ የሚለብሰውን ልብስ እንኳን ሊመርጥ በማይችልበት ደብዛዛ ብርሃን ከሴት ጋር በፍቅር ወድቋል፡፡

ሞሪስ ሼቫሊዬን

(ፈረንሳዊ ዘፋኝና ተዋናይ)

ጨዋታዋ ያለችው አንድ ሰው ማፍቀር ላይ ነው፡፡ አንድ ሰው ካፈቀርሽ ሌላውን ሁሉ በተቃራኒው መመልከት ትጀምሪያለሽ፡፡

ጄምስ ባልድዊን

(አሜሪካዊ ፀሐፊና የሲቪል መብት ተሟጋች)

ፍቅር ካከተመ በኋላ መፋቀራቸው የማያሳፍራቸው በጣም ጥቂት ሰዎች አሉ፡፡

ፍራንሶይስላ ሮቼፎካልድ

(ፈረንሳዊ የአባባሎች ፀሐፊና የሥነምግባር ሊቅ)

ሁለት ነፍሶች በአንድ፤ ሁለት ልቦች አንድ ልብ ውስጥ፡፡

ጉይላዩም ዱ ባርታስ

(ፈረንሳዊ ገጣሚ)

እኔና እናትሽ ተጋብተን ቢሆን ኖሮ ለረዥም ጊዜ በደስታ የምንኖር ይመስልሻል?

ጆን ጌይ

(እንግሊዛዊ ገጣሚና ፀሐፊ ተውኔት) The Dagger’s opera

በፍቅር ላይ ዲሞክራሲ ሲተገበር ዝሙት ይባላል፡፡

ኤች.ኤል.ሜንከን

(አሜሪካዊ ጋዜጠኛ፣ ሃያሲና አርታኢ)

ሚስቶች፤ ለጐረምሳ ወንዶች ውሽሞች፣ በመካከለኛ እድሜ ላሉት ጓደኞች፣ ለሽማግሌዎች ሞግዚቶች ናቸው፡፡

ፍራንሲስ ቤከን

(እንግሊዛዊ ፈላስፋ፣ ከፍተኛ ባለስልጣንና ጠበቃ)

ብዙ ሴቶችን በመጐምዠት አይቼአለሁ፡፡ በልቤ ብዙ ጊዜ ዝሙት ፈፅሜአለሁ፡፡ እግዚአብሔር ለዚህ ይቅር ይለኛል፡፡

ጂሚ ካርተር

(የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩ ለplayboy በሰጡት ቃለምልልስ)

ካገቡ ወንዶች ጋር አንሶላ አልጋፈፍም ስል በትዳራቸው ደስተኛ ሆነው ከሚኖሩ ወንዶች ጋር አልተኛም ማለቴ ነው፡፡

ብሪት ኡክላንድ

(ስዊድናዊ የፊልም ተዋናይ)

 

 

Read 5416 times Last modified on Saturday, 21 January 2012 11:02