Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 21 January 2012 11:13

ማርክ ዎልበርግ ቢሮ የመክፈት ፍላጐት የለውም

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ታዋቂው የፊልም ባለሙያ ማርክ ዎልበርግ ቢሮ ከፍቶ የመስራት ፍላጎት እንደሌለው ተናገረ፡፡ ባለፈው ሳምንት ለእይታ የበቃው ‹ኮንትራባንድ› የተባለው ፊልሙ በሰሜን አሜሪካ ብቻ 24 ሚሊዮን ዶላር በማስገባት በቦክስ ኦፊስ ሳምንታዊ የገቢ ደረጃ አንደኛ ሲሆን፤ ፊልሙ በ25 ሚሊዮን ዶላር በጀት የተሰራ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ተዋናይና ፕሮዲውሰሩ ማርክ ዎልበርግ፤ በሆሊውድ ትርፋማ ከሚባሉ ባለሙያዎች አንዱ ሲሆን በመልካም ባህርይው፤ በአርአያነት በሚጠቀስ የቤተሰብ ህይወቱ እና በታታሪነቱ ይታወቃል፡፡ ማርክ ስራዎቹን ሲያከናውን  የሚያርፍበትን የቤቨርሊ ሂልስ ሆቴል እንደቢሮ በመጠቀምና ብላክቤሪ ስልኩን እንደ ሰራተኛ በመገልገል የመስራት ባህልን  ማዳበሩንም ተናግሯል፡፡ በፊልም ፕሮዲውሰርነት ብዙ ስክሪፕቶችን አዘውትሮ የማንበብ ዕድል እንዳለው የሚናገረው ማርክ ዎልበርግ፤ ራሱ በዲያሬክተርነት የሚሰራበትን የፊልም ፅሁፍ እያፈላለገ እንደሆነም ገልጿል፡፡ በሚቀጥሉት 18 ወራት ማርክ ዎልበርግ በሦስት ምርጥ ፊልሞች ላይ በመሪ ተዋናይነት እንደሚሰራ የገለፀው ኢንተርቴይመንት ዊክሊ፤ በተለይ “ብሮክን ሲቲ” በተባለ የወንጀል ድራማ ላይ ከራስል ክሮውና ከካተሪን ዜታ ጆንስ ጋር በመተወን የሚሰራው ፊልም በጉጉት የሚጠበቅ እንደሆነ አመልክቷል፡፡

 

 

Read 2228 times Last modified on Saturday, 21 January 2012 11:14