Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 21 January 2012 11:15

“ሼፉ” ፊልም ለዕይታ ቀረበ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

“እስከ መቼ” የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን ተከፈተ

“ሼፉ” የተሰኘው የፍቅር ኮሜዲ ፊልም ባለፈው ሰኞ በብሔራዊ ቲያትር ተመረቀ፡፡ በካም ግሎባል ፒክቸርስ የተሰራው 1፡40 የሚፈጀው ፊልም አንድ ዝነኛና ሃብታም ሼፍ በአጋጣሚ ከተዋወቃት የጨርቆስ ልጅ ጋር የሚያሳልፈውን የፍቅር ታሪክ ያሳያል፡፡ በዚህ ፊልም ላይ አርቲስት ተስፋዬ ገሠሠ፣ ማህደር አሰፋ፣ ሚካኤል ሚሊዮን፣ አለምሰገድ ተስፋዬ እና ሌሎችም ተዋናዮች የተሳተፉበት ሲሆን ለተመልካች መታየት መጀመሩን የፊልሙ ፕሮዲዩሰር ኪሩቤል አሰፋው ገልጿል፡፡ የፊልሙ ደራሲ ሚካኤል ይበይን ሲሆን አዘጋጁ መሐመድ ዳውድ ነው፡፡ በሌላ በኩል በፎቶ ጋዜጠኛ ሲሳይ ጉዛይ የተነሱ አስከፊ የትራፊክ አደጋዎችን የሚያሳይ የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን ትላንት በብሄራዊ ቴአትር ተከፍቷል፡፡ “እስከመቼ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን፤ ለሶስት ቀናት ለተመልካች ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ተጠቁሟል፡፡

 

 

Read 2517 times Last modified on Saturday, 21 January 2012 11:16