Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 21 January 2012 11:16

የቅጂ መብት የጣሱ ተቀጡ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የኢትዮጵያ ኦዲቪዥዋል አሳታሚዎች ማህበር፤ የቅጂና ተዛማጅ መብቶች የጣሱ ሁለት ግለሰቦች በፍርድ ቤት መቀጣታቸውን ገለፀ፡፡ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ 15 ሕገወጥ ቅጂዎች የተገኙባቸው አቶ ጴጥሮስ ተፈራ እና 41 ቅጂዎች የተገኘባቸው አቶ ዳንኤል ወንድወሠን በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት እያንዳንዳቸው በአምስት ዓመት ፅኑ እስራትና ሁለት ዓመት ከሕዝባዊ መብቶች በመታገድ እንደተቀጡ ታውቋል፡፡ የማህበሩ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ወይዘሪት ብፅአተ ገብረፃድቅ ስለቅጣቱ ለአዲስ አድማስ ሲናገሩ፤ የተገኘው ሕገወጥ ቅጂ መብዛትና ማነስ በውሳኔዎቹ ላይ ተፅእኖ የለውም፣ ትንሽም ብዙም የተገኘበት በማስረጃ ተረጋግጦ ይቀጣል፤ ፍርድ ቤቶች በጣም ተባባሪዎች ናቸው ብለዋል፡፡

 

 

Read 1743 times Last modified on Saturday, 21 January 2012 11:17