Print this page
Sunday, 10 May 2015 14:14

የቱርክ ባለሀብቶች በኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሊሰማሩ ነው

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(2 votes)

በኤሌክትሮኒክስና ኤሌክትሪካል ዘርፍ የተሰማሩ የቱርክ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በትራንስፎርመርና
    ሌሎች የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ማምረት ተግባር ላይ ሊሰማሩ ነው፡፡ ዋፋ ማርኬቲንግ ፕሮሞሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከቱርክ ኤሌክትሮ ቴክኖሎጂ ላኪ ማህበርና ከቱርክ ሴምባሲ ንግድ ካውንስል ጋር በመተባበር ሰሞኑን በሸራተን አዲስ አዘጋጅቶት በነበረው የንግድ የገበያ ትስስር መፍጠሪያ መድረክ ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጅነር አዜብ አስናቀ እንደተናገሩት፤ ባለሀብቶች በኤሌክትሮ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ ለመሳተፍ ፍላጐት ማሳየታቸው፣ አገሪቱ በዘርፉ እያካሄደች ላለችው እንቅስቃሴ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል፡፡ ቀደም ሲል በኤሌክትሮኒክስና ኤሌክትሪካል ዕቃዎች ላይ ይታያል የሚባለው የጥራት ችግር እንደማይኖር የገለፁት ኢንጅነሯ፤ ዕቃዎቹ እዚሁ አገራችን ውስጥ መመረታቸው እንዲህ አይነት ችግሮች በሚገጥሙ ጊዜ ፈጣን የእርምት እርምጃ ለመውሰድ እንድንችል ያደርገናል ብለዋል፡፡ በጥራት ጉዳይ ከፍተኛ የቁጥጥር ሥራ እንደሚሰራም ኢንጅነር አዜብ ገልፀዋል፡፡
ሰሞኑን በሸራተን አዲስ የተካሄደው ይኸው የሁለቱ አገራት ባለሀብቶች የንግድ ለንግድ የገበያ ትስስር ከቀናት በፊት በቱርክ የተካሄደው የንግድ ትስስር መፍጠሪያ መድረክ ቀጣይ ፕሮግራም እንደሆነና መድረኩ የኢትዮጵያ ባለሀብቶች ከቱርክ ባለሃብቶች ጋር በጋራ ለመሥራት እንዲችሉ በእጅጉ እንደሚያግዛቸው የዋፋ ማርኬቲንግ ፕሮሞሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፋንታዬ ጌታነህ ገልፀዋል፡፡  

Read 2111 times