Tuesday, 26 May 2015 08:00

“በራሪ መኪኖች” በ2 አመት ጊዜ ውስጥ ለገበያ ይበቃሉ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

       አንድ በራሪ መኪና 566 ሺህ ዶላር ተተምኗል

      በርካታ ቁጥር ያላቸው የመኪና አምራች ኩባንያዎች በራሪ መኪናዎችን በማምረት ቀድመው ለገበያ ለማቅረብ ብርቱ ፉክክር ውስጥ እንደሚገኙና መኪኖቹ በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ ለገበያ ይቀርባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ሲኤንኤን ዘገበ፡፡

በአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪው ዘርፍ መሰረታዊ ለውጥ ይመጣበታል ተብሎ በሚነገርለት የበራሪ መኪናዎች ፈጠራ ፉክክር ውስጥ ቴራፉጊያ፣ ኤሮሞቢልና ሞለር ኢንተርናሽናልን ጨምሮ በርካታ የተለያዩ አገራት የመኪና አምራች ኩባንያዎች እየተፎካከሩ እንደሚገኙ ዘገባው ጠቁሟል፡፡

የአሜሪካው ቴራፉጊያ ኩባንያ  በራሪ መኪናዎችን በሁለት አመታት ጊዜ ውስጥ አምርቶ ለገበያ ለማቅረብ እየተዘጋጀ እንደሚገኝ የጠቆመው ዘገባው፣ ኩባንያው ከ100 በላይ ደንበኞቹ የግዢ ትዕዛዝ እንደተሰጠውና ከፊል ክፍያ እንደተፈጸመለት አመልክቷል፡፡

የስሎቫኪያው ኤሮሞቢል በበኩሉ፤ በ2017 መጀመሪያ ላይ የበራሪ መኪኖችን ዲዛይን ለማጠናቀቅና ከገዢዎች ትዕዛዝ ለመቀበል ያቀደ ሲሆን የግዢ ጥያቄ ከደንበኞቹ በመቀበል ላይ የሚገኘው የኔዘርላንዱ ፓል-ቪ ኩባንያም በ2017 አጋማሽ መኪኖቹን ለደንበኞቹ ለማስረከብ አቅዶ እየሰራ ይገኛል፡፡

ኩባንያዎቹ በሚያመርቷቸው በራሪ መኪኖች ትርፋማ እንደሚሆኑ ቅንጣት ታህል ጥርጣሬ ባይኖራቸውም፣ ከመንገድ ደህንነት ጋር የተያያዙና የአጭር ጊዜ ግቦቻቸውን ከማሳካት የሚገቷቸው በርካታ እንቅፋቶች ሊገጥሟቸው እንደሚችሉ እየተነገረ ነው፡፡

በራሪ መኪኖቹ በመንገድ ላይ በአግባቡ መንቀሳቀስ መቻላቸውንና ደህንነታቸውን ለመፈተሸ የሚደረጉላቸውን በርካታ ፈተናዎች ማለፍ እንደሚጠበቅባቸው የጠቆመው ዘገባው፤ ከየአገራቱ መንግስታት አስፈላጊውን የአቪየሽን፣ የመንገድና የትራንስፖርት ፈቃዶችን የማግኘቱ ጉዳይም ረጅም ጊዜን ሊወስድባቸው እንደሚችል እየተነገረ መሆኑን ገልጿል፡፡ ኩባንያዎቹ ለማምረት ያሰቧቸው በራሪ መኪኖች ዲዛይንና ለገበያ የሚያቀርቡበት  የመሸጫ ዋጋቸው የተለያየ ነው፡፡ የመኪኖቹ አማካይ ዋጋ 300 ሺህ ዶላር እንደሚደርስ ዘገባው ጠቁሞ፣ የፓል-ቪ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዲንጊ ማኔዝ፣ ኩባንያቸው አንዷን በራሪ መኪና የሚሸጥበት ከፍተኛው ዋጋ 566 ሺህ ዶላር እንደሚሆን መናገራቸውን አክሎ ገልጿል፡፡

Read 1482 times