Saturday, 06 June 2015 13:53

ሸራተን ሆቴልን ለ21 ዓመታት በስራ አስኪያጅነት ያገለገሉት ፈረንሳዊው ሥራ አስኪያጅ አረፉ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(2 votes)

 በኑዛዜያቸው መሠረት ኢትዮጵያ ውስጥ ይቀበራሉ
                
    ሸራተን አዲስ ሆቴል ከተከፈተ ጀምሮ ላለፉት 21 ዓመታት በዋና ሥራ አስኪያጅነት ያገለገሉት ፈረንሳዊው ሚስተር ዣን ፔሪ ማኒጎፍ ባደረባቸው ህመም በዋሺንግተን ሆስፒታል ህክምና ሲደረግላቸው ቆይተው በ65 ዓመታቸው ከትላንት በስቲያ አረፉ፡፡
የዴንማርክና የፈረንሳይ ትውልድ ያላቸው ሥራ አስኪያጁ፤ ላለፉት ዘጠኝ ወራት በአሜሪካ ዋሺንግተን ሆስፒታል ከፍተኛ ህክምና ሲከታተሉ መቆየታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሚስተር ማኒጎፍ ህይወታቸው ከማለፉ በፊት በኢትዮጵያ መቀበር እንደሚፈልጉ መናዘዛቸውን የጠቆሙት ምንጮች፡፡ በቀጣዩ ሳምንት አስከሬናቸው ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጣና ሥርዓተ ቀብራቸው እንደሚፈፀም ገልፀዋል፡፡

Read 3033 times