ፊልሞቹን በገዛ ገንዘቡ እንደሚሰራ የሚናገረው ባለሙያው፤ የሆሊውድ የፊልም ኩባንያዎች ለአዳዲስ ፊልሞች የፋይናንስ ድጋፍ ከማድረግ ይልቅ በተከታታይ እና በቴክኖሎጂ ቅንብር ለሚሰሩ ፊልሞች ላይ ማድላታቸው ያሳዝናል ብሏል፡፡በሌላ በኩል ባለፉት በሆሊውድ የፊልም ኢንዱስትሪ ባለፉት 13 ዓመታት የሴት ዲያሬክተሮች ተሳትፎ በግማሽ እንደቀነሰ “ሴንተር ፎር ዘ ስተዲ ኦፍ ውመን ኢን ቴሌቭዥን ኤንድ ፊልም” የተሰኘው ተቋም ያወጣውን ሪፖርት ጠቅሶ የዘገበው ሎስ አንጀለስ ታይምስ፤ ሴት ባለሙያዎች የዶክመንታሪ፣ ድራማ እና የኮሜዲ ጭብጥ ባላቸው ፊልሞች ላይ መጠነኛ ተሳትፎ ቢኖራቸውም በሆረር፣ አክሽንና አኒሜሽን ፊልሞች ላይ የመስራት እድላቸው ዝቅተኛ እንደሆነ አመልክቷል፡፡ አምና ከታዩ ፊልሞች 94 በመቶ ያህሉ በወንድ ዲያሬክተሮች መሰራታቸውን የጠቆመው ሪፖርቱ፤ በሆሊውድ የፊልም ስራ መስኮች ሴቶች ያላቸው ድርሻ ዝቅተኛ ነው ብሏል፡፡ የሆሊውድ ፊልም ኩባንያዎች፤ በሴቶች የሚሰሩ ፊልሞች የገበያ ስኬት ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው የገለፀው ሪፖርቱ፤ ሴቶች ከፊልም ፀሃፊዎች 14 በመቶ፤ ከከፍተኛ ፕሮዲውሰሮች 18 በመቶ፤ ከፕሮዲውሰሮች 25 በመቶ፤ ከኤዲተሮች 20 በመቶ እንዲሁም ከሲኒማቶግራፈሮች አራት በመቶ ድርሻ አላቸው ብሏል፡፡