Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 28 January 2012 13:43

ሳምንቱ የ”አንደርዎርልድ፡ አዌክኒንግ” ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በቫምፓየር እና ዌርውልፍ መካከል ያለውን የዘመናት ግጭት ተንተርሶ ሰዎች እነዚህን ፍጥረታት ለማደን የሚያደርጉትን ዘመቻ የሚተርከው “አንደርዎርልድ፡ አዌክኒንግ” የተሰኘው ሆረር ፊልም የቦክስ ኦፊስን የገቢ ደረጃ እየመራ ነው፡፡ ፊልሙ ባለፈው ሳምንት በሰሜን አሜሪካ 2223 ሲኒማ ቤቶች የታየ ሲሆን 25.3 ሚሊዮን ዶላር አስገብቷል፡፡ ሶኒ ፒክቸርስ በ70 ሚሊዮን ዶላር በጀት የሰራው “አንደርዎርልድ፡ አዌክኒንግ” አራተኛውና የመጨረሻው የፊልሙ ክፍል ሲሆን ከቀዳሚዎቹ ፊልሞች የሚለየው በ3ዲ  በመሰራቱ ነው፡፡ ፊልሙን በመሪ ተዋናይነት የሰራችው ኬት ቤኪንሴል፤ በመጀመርያዎቹ ሁለት ፊልሞች ላይ ከሰራች በኋላ በሶስተኛው ተቀይራ አራተኛው የፊልሙ ክፍል ላይ ተመልሳ እንደተወነች ታውቋል፡፡ ባለፉት ስምንት ዓመታት የታዩት ሦስት የፊልሙ ክፍሎች በመላው ዓለም 298.4 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንዳስገኙ ቦክስ ኦፊስ ሞጆ አመልክቷል፡፡

 

 

Read 1579 times Last modified on Saturday, 28 January 2012 13:47