Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 28 January 2012 13:47

ዊትኒ ሂዩስተን “ችስታ” ሆናለች

Written by 
Rate this item
(2 votes)

በአደንዛዥ እፅ ሱሰኝነት ህይወቷ የተቃወሰባት የ48 ዓመቷ ድምፃዊትና የፊልም ተዋናይት ዊትኒ ሂዩስተን 100 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ሃብቷን አሟጥጣ ጨርሳ ችስታ እንደሆነች ዴይሊ ሜል ዘገበ፡፡ ዊትኒ በሙዚቃ አሳታሚዋ አሪስታ ሪኮርድስ ችሮታ ለከፋ የኑሮ ችግር ሳትጋለጥ እንደቆየች የዘገበው ዴይሊ ሜል፤ ጓደኞቿን ከመቶ ዶላር ጀምሮ እየተበደረች ህይወቷን እየገፋች ነው ብሏል፡፡ ዊትኒ ጓደኞቿ እርዳታ ባያደርጉላት ኖሮ መኖርያ ቤት እንኳን አይኖራትም ነበር ያለው ዴይሊ ሜል፤ አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ በግልፅ የሚታወቅ ነገር የለም ብሏል፡፡ የዊትኒ ሂዩስተን ቃል አቀባይ በበኩሉ “ቸስታለች” ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ፍፁም ሃሰት ነው በማለት ያስተባበለ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ሁለት ፊልሞች ፕሮዲዩስ ማድረጓንና በከፍተኛ ጉጉት የሚጠበቅ የሙዚቃ አልበሟን ሰርታ ማጠናቀቋን ገልጿል፡፡

Read 1821 times Last modified on Saturday, 28 January 2012 13:51