Print this page
Saturday, 28 January 2012 14:00

የጐንደር ቁንጅና ውድድር ተጠናቀቀ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

በጐንደር ከተማ ሲካሄድ የሰነበተው የቁንጅና ውድድር ባለፈው እሁድ ምሽት ተጠናቀቀ፡፡ ሴቶች “ብርሃን ሞገሳ” ወንዶች “ጐንደር ሰገድ” በሚል ርእስ የተካሄደውን ውድድር ያዘጋጀው ሚራል ሥነ ጥበብና ሞዴሊንግ ማሰልጠኛ ማዕከል ሲሆን የ”ኢትዮጵያን በጐንደር ብሔራዊ ትዕይንት” ዝግጅት አካል መሆኑን የትዕይንቱ አስተባባሪ ሀገሬ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ሄኖክ ስዩም ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ 52 ተወዳዳሪዎች በተሳተፉበት ውድድር ኤደን ስለሺ “ወይዘሪት ብርሃነ ሞገሳ፣ መሠረት አዱኛ ሁለተኛ፣ ሀና ይዘዝ ሦስተኛ ሆነዋል፡፡ በወንዶች ውድድርም ግደይ ማሙነህ የ”ጐንደር ሰገድ”ነት ዘውዱን ሲቀዳጅ ዘላለም ዓለምሰገድ ሁለተኛ አሰፋ ግርማ ሦስተኛ ወጥተዋል፡፡ በሁለቱ ዘርፎች ባህላዊ የቁንጅና ውድድር ከአንድ እስከ ሦስት የወጡት ቆነጃጅት የገንዘብ ሽልማት ተደርጐላቸዋል፡፡

 

 

Read 1650 times Last modified on Saturday, 28 January 2012 14:04