Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 28 January 2012 14:05

ተልዕኮ” ምጽአት “ልቦለድ ሃሙስ ይመረቃል የንጋት ሹክሹክታዎች ለንባብ በቃ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በጋዜጠኛና ደራሲ ካሳ አያሌው ካሳ የተዘጋጀው “ተልዕኮ ምጽአት” ረዥም ልቦለድ መጽሐፍ በመጪው ሐሙስ ምሽት በኢትዮጵያ ሆቴል ይመረቃል፡፡ ከማክሰኞ ጀምሮ ገበያ ላይ በሚውለው መጽሐፍ ምርቃት ላይ የመንግስት ኮሙኒከሽን ጉዳዮች ኃላፊ ሚኒስትር አቶ በረከት ስምኦን እና በሚኒስትር ማዕረግ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይ ፀሐዬ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ 20 ምዕራፎችን በ211 ገፆቹ የያዘው መጽሐፍ ለንባብ የበቃው ለሀገር ውስጥ በ40 ብር ለውጭ ሀገራት በ25 የአሜሪካ ዶላር ነው፡፡ የሕትመቱን ውጣ ውረድ አስመልክቶ ከአዲስ አድማስ ማብራርያ የጠየቀው ደራሲ “ውይ …ውይ…የተንገላታሁበት ነው፡፡

ከታተመው ስድስት ሺህ ቅጂ የሦስት ሺሁን የEMAY አሳታሚ ሥራ አስኪያጅ አቶ የማነ ግርማይ አግዘውኛል፡፡” ብሏል፡፡ ልቦለዱ ታቦተ ጽዮንን ከኢትዮጵያ ለማሸሽ በተደረጉ ጥረቶችና በአባይ ጉዳይ ላይ በተሰሩ ወንጀሎች ላይ ያተኮረ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ ነው ብሏል ካሳ ስለመጀመሪያ መጽሐፉ ሲናገር፡፡ካሳ አያሌው በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት (ሬዲዮ ፋና) ሞጋችና ግድፈት ፈልፋይ በሆነው “ተጓዥ ነቃሽ” ፕሮግራሙ ይታወቃል፡፡ በሌላም በኩል በተስፋዬ አየለ የተዘጋጀው “የንጋት ሹክሹክታዎች “የግጥም መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ 95 ገፆች ያሉት መጽሐፍ በጅማ ከተማ የታተመ ሲሆን ዋጋውም 18 ብር ነው፡፡

 

 

 

Read 1637 times Last modified on Saturday, 28 January 2012 14:10