Saturday, 28 January 2012 14:06

ሳያትና ሰይፉ በሽምግልና ተስማሙ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

ድምፃዊት፣ ተዋናይና ሞዴል ሳያት ደምሴና ጋዜጠኛ ሰይፉ ፋንታሁን በዘገባ ስም ማጥፋት ተመስርቶ የነበረ ክሳቸውን በሽምግልና ጨርሰናል በዚህም ጉዳዩ ፍርድ ቤት ደርሶ ስንከራከርበት ብንቆይም ለሌሎች ወገኖች የሚያስተላልፈው መልእክት ይኖራል በማለት በሽምግልና ጨርሰናል ብለዋል፡፡ ከትናንት ወዲያ ጠዋት በሐርመኒ ሆቴል በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ከሁለቱ ሌላ የሽምግልና ተነሳሽነቱን አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬ፣ የሕግና ባለሙያ ቤተልሄም ደምሴ እና ሌሎችም ወስደው ክሱ በመግባባት ተቋጭቷል ብለዋል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ የተናገረው ሰይፉ የሳያትን አስተያየት ሳናካትት በሰራነው ዘገባ ተሳስተናል ሳያት በሲዲ አልዘፈነችም ሜጀር ግን ወርዷል” ሲል ይቅርታ ጠይቋል፡፡

ይቅርታውን የተቀበለችው ሳያት “በፊቱንም ከሰይፉ ጋር የግል ጠብ የለኝም በዝግጅቱ ላይ እንግዳ ቢያደርገኝም እጋበዛለሁ” ብላለች፡፡ በሰይፉ ዘገባ ምክንያት ከሰይፉ “ታዲያስ አዲስ” ዝግጅት አቅራቢነትን ስለተውት ባልደረቦቹ የተጠየቀው ሰይፉ “ፕሮግራሙን ሳይጨርሱ በመውጣቸው ሸገር ኤፍ ኤም ቀጣቸው ለመቀጣት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው እንጂ ከኔ ጋር አይደለም” ብሏል፡፡ የዘገባው ምን ያህል እንደጐዳት ከአዲስ አድማስ የተጠየቀችው ድምፃዊት ሳያት በጣም ጐድቶኛል ሆኖም እንደዘገባው አለመሆኔን በሥራዬ አረጋግጣለሁ፡፡” ብላለች፡፡

 

Read 1759 times Last modified on Saturday, 28 January 2012 14:10