Print this page
Saturday, 04 February 2012 11:38

የአፍሪካ ዋንጫው

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

ሩብ ፍፃሜ ዛሬ ይጀመራል

የሽልማቱ ማነስ አነጋጋሪ ሆኗል

ለአውሮፓ ደላሎች የመመልመልያ መድረክ ነው

ሱዳን ሴካፋን እንድታነቃቃ አድርጓል

የ28ኛው አፍሪካ ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ዛሬ ሲጀመር ዛምቢያ ፤ኮትዲቯር፤ ጋቦንና ጋና በምድብ ማጣርያው ባሳዩት ጠንካራ አቋም ለዋንጫው ከፍተኛ ግምት ሲወስዱ ቀሪዎቹ አራት ቡድኖች ኢኳቶርያል ጊኒ፤ ቱኒዚያ ሱዳንና ማሊ በሁለተኛ ደረጃ ለሻምፒዮናነቱ ግምት ተጠብቀዋል፡፡  ሩብ ፍፃሜው በወደብ ከተማዋ ባታ ዛምቢያና ሱዳን በሚያደርጉት ፍልሚያ ሲጀመር በዋና ከተማዋ ማላቦ ደግሞ አዘጋጇ ኢኳቶርያል ጊኒ ታላቋን ኮትዲቯርታስተናግዳለች፡፡ ነገ ደግሞ ሌላዋ አዘጋጅ ጋቦን በሊበርቪሌ  ከማሊ ጋር ስትገናኝ በሌላ ጨዋታ በፍራንኪቬል ላይ ጋና እና ቱኒዚያ ይጫወታሉ፡፡ ለሩብ ፍፃሜ ከበቁት ቡድኖች አራት ጊዜ በማሸነፍ ጋና በከፍተኛ ወጤት ስትመራ አንዳንድ ጊዜ ያሸነፉት ደግሞ ቱኒዚያ እና ሱዳን ናቸው፡፡ ዛምቢያና ማሊ በተሳትፎ ታሪካቸው እኩል 1 ግዜ ሁለተኛ ደረጃ ያገኙ ሲሆን ጋቦን ለሁለተኛ ጊዜ ሩብ ፍፃሜ ስትደርስ ኢኳቶርያል ጊኒ ለመጀመርያ ጊዜዋ ለዚህ ደረጃ እንደበቃች ታውቋል፡

፡ከሩብ ፍፃሜው በፊት በተደረጉት የምድብ ማጣርያ 24 ጨዋታዎች በሁለቱ አዘጋጅ አገራት ስታድዬሞች 361ሺ 632 ተመልካች የታደመ ሲሆን 61 ጎሎች ከመረብ ሲያረፉ በእያንዳንዱ ጨዋታ በአማካይ 2.54 ጎል ሲመዘገብ ቆይቷል፡፡ በኮከብ ግብ አግቢነቱ ፉክክር የአንጎላው ማኑቾ፤ የጋቦኑ አቡሜያንግና የቱኒዚያው ሁሴኒ ካሂራ በእኩል 3 ጎሎች ተናንቀዋል፡፡የዋንጫው ክብር በሽልማቱ ማነስ መደብዘዙበ2001 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ያነሳው የጋናው ሳሚ ኩፎር ለአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ የሚሰጠው የገንዘብ ሽልማት ቀልድ ብሎታል፡፡ ለአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ የሚሰጠው የሽልማት ገንዘብ 2 ሚሊዮን ዶላር መሆኑ ለዋንጫው መሰጠት ያለበትን ክብር አደብዝዞታል እየተባለ ነው፡፡ ከ2 ዓመት በፊት ደቡብ አፍሪካ ባስተናገደችው የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮን የሆነችው ስፔን  31 ሚሊዮን ዩሮ መቀበሏ ይታወሳል፡፡  በስፖርቱ ዓለም ከፍተኛው የሽልማት ገንዘብ የሚቀርበው በፊፋ የሚዘጋጀው ዓለም ዋንጫ ላይ ሲሆን ተሳታፊ የሚሆኑ 32 ብሄራዊ ቡድኖች ከ280 ሚሊዮን ዶላሩ የየራሳቸው ዳጎስ ያለ ድርሻ ይኖረቸዋል፡፡ በዋንጫ ድል ከፍተኛ ሽልማት የሚሰጠው ደግሞ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ላይ ሲሆን ሻምፒዮኑ እስከ 170 ሚሊዮን ዶላር ሲያገኝ  2ኛ ደረጃ ያገኘው ደግሞ 60 ሚሊዮን ዶላር ይታሰብለታል፡፡ የአፍሪካ ዋንጫ ሽልማት ከእነዚህ ሽልማቶች ጋር ሲነፃፀር እጅግ ያነሰ ይሆናል፡፡ፎር ለብሄራዊ  ቡድን 2 ሚሊዮን ዶላር መስጠት ተገቢ አይደለም ሲል የአውሮፓ እግር ኳስ ከአፍሪካ ልጆች በሚጠቀመው ገቢ አንፃር ይህን ለማሻሻል ድጋፍ ማድረግ አለበት ብሏል፡፡ የአፍሪካ ሻምፒዮን ቢያንስ 10 ሚሊዮን ዶላር ሊሰጠው እንደሚገባም  ሃሳብ አቅርቧል፡፡ አውሮፓ ደላሎች ደፈጣውድድሩ ለአውሮፓ እግር ኳስ ክለቦችና ደላሎቻቸው የመመልመያ መድረክ ሆኗልም እየተባለ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም የአፍሪካ ልጆች በአውሮፓ ክለቦችገና በታዳጊነታቸው እየተጠለፉ የአህጉሪቱ እግር ኳስ አደጋ ላይ ወደቀ በሚልም ምሬት በዝቷል፡፡  የአፍሪካ ዋንጫው በአውሮፓ ትልልቅ ሊጎች በሚወዳደሩ ክለቦች ያሉታዳጊተጨዋቾችንማስኮብለሉ የየአገራቱን እድገት እያንቀራፈፈ ነው የሚለው ጉዳይ ዘንድሮም ከፍተኛ ውዝግብ ፈጥሯል፡፡ በሺዎች የሚገመቱ አፍሪካውያን በአውሮፓ ክለቦች ይጫወታሉ፡፡ ይህም በአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች የሚደረጉ ጨዋታዎችን ተወዳጅነት በአፍሪካ  እንዲስፋፋ ምክንያት ሆኗል፡፡ ባለፈው ዓመትንሲውመር ሳይት አፍሪካ የተባለ የገበያ ጥናት ተቋም ይፋ ባደረገው ሪፖርት በአፍሪካ እጅግ ዝነኛ እና ተወዳጅ ክለብ ብሎ ያስቀመጠው አርሰናልን ሲሆን ማን ዩናይትድ፤ ቼልሲና ሊቨርፑል ተከታታይ ደረጃ አግኝተዋል፡፡ ይሄው የአውሮፓ የክለብ እግር ኳስ ተወዳጅነትና የአፍሪካዊያን ፕሮፌሽናል ተጨዋቾች ሚና የሁለቱን አህጉራት የእግር ኳስ ግንኙነት ይበልጥ ያስተሳሰረው ሆኗል፡፡የአውሮፓ ክለቦች ከአፍሪካ በሚወስዷቸው ተጨዋቾች ከፍተኛ እምነት እንዳላቸው በአህጉሪቱ የእግር ኳስ እድገት ላይ ያደረጉት ኢንቨስትመንትም ይመሰክራል፡፡ ከእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ክለቦች ማን ዩናይትድና ቦልተን የእግር ኳስ ትምህርት ቤቶችን በአፍሪካ ከፍተዋል፡፡ ከሆላንድ ክለቦች ክለብ  በጋና ዋና ከተማ አክራ አካዳሚ እየከፈተ ሲሆን አያክስ ደግሞ በደቡብ አፍሪካ ሊግ የሚወዳደር አያክስ ኬፕታውን የተባለ ክለብን ያስተዳድራል፡፡ ታላላቆቹ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ክለቦች ማን ዩናይትድ፤ አርሰናልና ቼልሲ በአፍሪካ ብዛት ባላቸው የደጋፊ ቡድኖቻቸውም የገበያ አቅም ይመካሉ፡፡የተባበሩት መንግስታት ወይስ ኢኳቶርያል ጊኒሌላውየአፍሪካ ዋንጫው አነጋጋሪ የሆነበት ጉዳይ ከአዘጋጆቹ አንዷ የሆነችው ኢኳቶርያል ጊኒ በቡድኗ በርካታ ዜግነታቸውን የቀየሩ ስፖርተኞች ከማሰለፏ ጋር በተያያዘ የተነሳው ነው፡፡ አጠቃላይ የህዝብ ብዛቷ 700ሺ የሚደርሰው ኢኳቶርያል ጊኒ ብራዚላዊ ግብ ጠባቂ፤ ላይቤሪያዊ ተከላካይ፤ አይቮራዊ አማካይ ፤ ካመሮናዊ አጥቂና በርካታ ስፔናውያን በድምሩ 13 ዜግነታቸውን የቀየሩ ተጨዋቾች አሰልፋ የተባበሩት መንግስታት ተብላለች፡፡ ኢኳቶርያል ጊኒ በአፍሪካ ዋንጫው ዝቅተኛው የእግር ኳስ ደረጃ ያላት አገር ብትሆንም ወደ ሩብ ፍፃሜው በማለፍ የመጀመርያዋ ቡድን ሆናለች፡፡ ይሄው የኢኳቶርያል ጊኒ አስደናቂ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ዜግነታቸውን በቀየሩ ተጨዋቾች የተገኘ መሆኑ ብሄራዊ ክብርን ያሟጥጣል በሚል መላው አህጉሪቱን ያከራከረ አጀንዳ ሆናል፡፡ የኢኳቶርያል ጊኒ ቡድን በማበረታቻው የሚለይ ሲሆን የፕሬዝዳንቱ ልጅ ቡድኑ ባሸነፈበት እያንዳንዱ ጨዋታ 1 ሚሊዮን ዶላር ጎል ለሚያገቡ ደግሞ 20ሺ ዶላር ቦነስ የሚሰጠው ነው፡፡ በርካታ ስፖርት አፍቃሪዎች ዜግነታቸውን በቀየሩ ተጨዋቾች ብሄራዊ ቡድኖች በዓለም አቀፍ ውድድሮች መሳተፋቸው የፉክክርን መንፈስ በማቀዝቀዝና በየአገራቱ ያለውን እድገት በማጓተት አሉታዊ ተፅእኖ ያሳድራል ይላሉ፡፡ አንዳንድ መረጃዎች በአውሮፓ አገራት ከ400 በላይ ዜግነታቸውን የቀየሩ አፍሪካውያን ተጨዋቾች መኖራቸውን ያመለክታሉ፡፡ ፊፋ የተጨዋቾች የዜግነት ቅየራ ስላሳሰበው አንድ ስፖርተኛ ዜግነቱን ለሚቀይርለት አገር ከመሰለፉ በፊት በዚያው አገር ለሁለት ዓመት እንዲኖር የሚጠይቀውን ቅድሚያ መስፈርት ወደ አምስት አመት ማራዘሙ ይገለፃል፡የሱዳን ድልበአፍሪካ ዋንጫው የሴካፋ ዞንን የወከለችው ሱዳን በአስደናቂ ገድል ደምቃለች፡፡ በዚህ የአፍሪካ ዋንጫ የሱዳን ቡድን ከ42 ዓመት በዃላ የመጀመርያ ድሉን ከማስመዝገቡም በላይ ለሩብ ፍፃሜ በመድረስም ለውድድሩ ማለፍ ላቃታቸው የሴካፋ ዞን ቡድኖች ተሞክሮ የሚሆን ስኬት አስመዝግቧል፡፡ በአማካይ እድሜያቸው 24 የሆኑ ተጨዋቾች በብሄራዊ ቡድኑ መሰባሰባቸውና በቅድመ ዝግጅት  በከፍተኛ ትኩረት መሰራቱ ለሱዳን መጠናከር ምክንያት መሆኑን አሰልጣኙ ተናግረዋል፡፡  ብሄራዊ ቡድኑ ለአፍሪካ ዋንጫው ሲዘጋጅ ከአልበሽር ከፍተኛ የበጀት ድጋፍ ከማግኘቱም በላይ በኳታር ፌደሬሽንም መጠነ ሰፊ እገዛ ተደርጎለታል፡፡ የሱዳን ብሄራዊ ቡድን በአገር በቀል ተጨዋቾች ለሩብ ፍፃሜ ሲበቃም በ1996 በተመሳሳይ ቱኒዚያ ካገኘችው ስኬት ጋር ተስተካክሏል፡፡  ከቡድኑ ተጨዋቾች 16ቱ ደግሞ ምንም አይነት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ተመክሮ እንኳን የላቸውም፡፡ በ1959 እና በ1967 እኤአ በተደረጉ የአፍሪካ ዋንጫዎች ሁለተኛ ደረጃ አግኝቶ የነበረው የሱዳን ብሄራዊ ቡድን በ1970 እኤአ ዋንጫውን ማግኘቱን ታሪክ ያስታውሳል፡፡ በፊፋ የእግር ኳስ ደረጃ ሱዳን ከዓለም 102ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 26ኛ ናት፡፡ የሁለቱ የአገሪቱ ክለቦች አል ሂላልና ኤል ሜሪክ መጠናከር ብሄራዊ ቡድኑን ወደ ተሻለ ደረጃ አሳድጎታል፡፡

 

 

 

Read 1864 times Last modified on Saturday, 04 February 2012 11:43