Saturday, 01 August 2015 14:55

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ቡድን ለሉሲዎች ጥሩ መነቃቃት ፈጥሯል

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

 ከ2 ሳምንት በፊት በባሕር ዳር ስታዲዬም በተደረገው ጨዋታ ካሜሩንን ሁለት ለአንድ ያሸነፈው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ቡድን በኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ላይ መነቃቃት ፈጠረ፡፡ የወጣቶቹ ጥረት ለዋናው ብሄራዊ ቡድን ሉሲዎች የወደፊት ስኬት ተስፋ አሳድሯል፡፡
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድኑ በቀጣይ ዙር የሚገናኘው ከቡርኪናፋሶ አቻው ጋር ይሆናል፡፡ የቡርኪናፋሶ ቡድን ያለፈው አልጄሪያን 3 ለ 1 በማሸነፍ ነው፡፡
በ2016 እ.ኤ.አ ፓፓዋ ኒው ጊኒ 8ኛውን ከ20 ዓመት በታች የሴቶች የዓለም ዋንጫ ታስተናግዳለች አፍሪካ በሁለት አገራት ትወከላለች። ከኢትዮጵያ እና ከቡርኪናፋሶ ባሻገር ኢኳቶሪያል ጊኒ ከጋና፣ ናይጄሪያ ከናሚቢያና ከዲሞክራቲክ ኮንጎ አሸናፊ፣ ዛምቢያ ከደቡብ አፍሪካ በሌሎቹ የማጣሪያ ጨዋታዎች ይገናኛሉ። ለኢትዮጵያና ቡርኪናፋሶ አሸናፊ የመጨረሻው ዙር ማጣርያ ጨዋታ የሚሆነው ከኢኳቶርያል ጊኒ እና ከጋና አሸናፊ ጋር ነው፡፡

Read 1809 times