Print this page
Saturday, 04 February 2012 12:21

“አትላስ ሽረግድ” ክፍል ሁለት ፊልም ይሰራል

Written by  ግሩም ሰይፉ girumsport@gmail.com
Rate this item
(0 votes)

በአየን ራንድ የልቦለድ ታሪክ “አትላስ ሽረግድ” ላይ የተሰራው ክፍል ሁለት ፊልም በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዋዜማ ለእይታ እንደሚበቃ ዘ ሆሊውድ ሪፖርተር አስታወቀ፡፡ ፊልም ሰሪዎቹ እቅዳቸውን ያስታወቁት የአየን ራንድን 107ኛ ዓመት ልደት ሰሞኑን ሲያከብሩ ነው፡፡ የፊልሙ የመጀመርያ ክፍል በሃያሲዎች ዘንድ ተቀባይነቱ ያነሰ ቢሆንም ሁለተኛውን ክፍል ለመስራት መወሰኑን ያመለከተው ዘገባው፤ የመጀመርያው ክፍል በ20 ሚሊዮን ዶላር በጀት ተሰርቶ 4.6 ሚሊዮን ዶላር ማስገባቱ ውሳኔያቸው ላይ ተፅእኖ አለማሳደሩ ማስገረሙን አትቷል፡፡ በአየን ራንድ የተፃፈውን ባለ 1100 ገፅ የልቦለድ መፅሃፍ በሦስት ክፍሎች የመስራት ሃሳብ መኖሩን የጠቀሰው “ዘ ሆሊውድ ሪፖርተር”፤ ፊልሙ በገቢ ረገድ ምንም ባይሳካለትም ሰፊ የበጀት ድጋፍ እንደሚያገኝ አመልክቷል፡፡

 

 

Read 1238 times Last modified on Saturday, 04 February 2012 12:26