Print this page
Saturday, 04 February 2012 12:27

ዲኔሮ ትወና በቅቶታል ተባለ

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

ሮበርት ዲኔሮ ከሲኒማው ዓለም እየተገለለ ዝናውም እየተሸረሸረ መምጣቱን ዘ ሂንዱስታን  ታይምስ ዘገበ፡፡ የ68 ዓመቱ ዲኔሮ በመሪ ተዋናይነት የሚሰራበት ‹ኤን ዋይ 22› የፖሊስ ምርመራ ድራማዊ ፊልም ከወር በኋላ በሲቢኤስ  ጣቢያ በተከታታይ መቅረብ ይጀምራል፡፡ በተዋናይነት ፤በፕሮዲውሰርነትና በዲያሬክቲንግ ስራዎች የረጅም ጊዜ ልምድ ያለው ዲኔሮ በትላልቅ ፊልሞች የመስራት እድል ማጣቱን የጠቀሰው ዘ ሂንዱስታን ታይምስ፤ ምናልባትም  በቀሪ የህይወት ዘመኑ ከስድስት ልጆቹ እና ከሶስት የልጅ ልጆቹ ጋር ቢያሳልፍ ይሻለዋል ብሏል፡፡ ‹ፍሪላንሰርስ›፤ ‹ሬድ ላይትስ› እና ‹አናዘር ቡልሺት ናይት ኢን ሳክ ሲቲ› የተባሉት ሶስት ፊልሞች ዘንድሮ ዲኔሮ በትወና የተሳተፈባቸው ፊልሞች ናቸው፡፡

Read 1187 times