Saturday, 04 February 2012 12:38

“የማዕበል አሶች” ሊተረክ ነው

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

በደራሲና ጋዜጠኛ ዳንኤል ወርቁ የተዘጋጀው “የማዕበል አሶች” የተሰኘ የረዥም ልቦለድ መፅሐፍ በፋና ኤፍኤም 98.1 አዲስ አበባ ሊተረክ ነው፡፡ በተዋናይ አያሌው ገብረማርያምና ተዋናይት ሙሉ ኪዳኔ በየሳምንቱ እሁድ ምሽት ከ3፡30 ጀምሮ ለ45 ደቂቃ የሚተረከው መፅሐፍ፤ የሚቀርበው “ጥበብና እፎይታ” በሚል ፕሮግራም ነው፡፡ ስለትረካው የጠየቅነው ደራሲ ዳንኤል ወርቁ “አንዴ ብቻ ታትሞ 3ሺህ ኮፒ ስለተሸጠና ስላለቀ እንዲሁም የወጣቶች ታሪክ ስለሆነ ለትረካው ተመርጧል” ብሏል፡፡  ደራሲው ከ”ጥበብና እፎይታ” ዋና አዘጋጆች አንዱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

Read 1355 times Last modified on Saturday, 04 February 2012 12:40