Print this page
Saturday, 04 February 2012 12:41

“ልጓም” እና “ማንዴላ” ለንባብ በቁ በላንድስኬፕ አርኪቴክትነት የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ መፅሐፍ ተፃፈላቸው

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

ጭንቀትን አስመልክቶ የተፃፈው “ልጓም” የሥነልቦና መፅሐፈ ለንባብ በቃ፡፡ በከተማ አድማሱና ኃይለሚካኤል አድማሱ የተዘጋጀው ባለ 143 ገፅ መፅሐፍ በ25 ብር ወይም በ10 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡ ከደራሲዎቹ አንዱ በእንግሊዝ የሚኖር ሲሆን እዚህ ካለው ሌላኛ አዘጋጅ ጋር በመሆን በኢሜይል እየተላላኩ እንዳዘጋጁት ለማወቅ ተችሏል፡፡በሌላም በኩል በምርትነህ ታምራት የተሰባሰቡ የእንግሊዝኛ ጥቅሶች የያዘው “Mandela” የጥቅሶችና የማንዴላ አመራር አስተምህሮቶች መፅሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ 95 ገፆች ያሉት መፅሐፍ ለገበያ የቀረበው በ20 ብር ነው፡፡በሌላም በኩል በላንድስኬፕ አርክቴክቸርነት የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ የተባለላቸው ኢንጂነር ጌታቸው ማህተመ ሥላሴ መፅሐፍ ተፃፈላቸዉ፡፡ በእመቤት ዘውዴ የተዘጋጀው ባለ 156 ገፅ መፅሐፍ በፎቶ ግራፎች ጭምር የተደገፈ ሲሆን ዋጋውም 35 ብር ነው፡፡ አዘጋጇ በመግቢያዋ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲን የሆኑትን ብፁዕ ዶር.አቡነ ጢሞቴዎስንና አስተዳደራቸውን ላደረጉት ድጋፍ አመስግናለች፡፡

 

 

Read 1343 times Last modified on Saturday, 04 February 2012 12:43