Print this page
Saturday, 11 February 2012 09:01

ራድክሊፍ ለኦስካር ግድ የለኝም አለ

Written by  ግሩም ሰይፉ girumsport@gmail.com
Rate this item
(0 votes)

የኦስካር እጩዎች ምሳ ተጋበዙ

በስምንት ተከታታይ ክፍሎች በተሰራው የሃሪ ፖተር ፊልም ላይ በመሪ ተዋናይነት የሰራው  ዳንኤል ራድክሊፍ ለኦስካር ሽልማት ግድ የለኝም ሲል መናገሩን ቢቢሲ አስታወቀ፡፡ የኦስካር ሽልማት ሰጭዎች አዋጭና ጭብጣቸው ለህፃናት በሚሆኑ ተወዳጅ ፊልሞች ላይንደሚያተኩሩተናገረው ዳንኤል ራድክሊፍ፤ ተወዳጅ የሃሪ ፖተር ፊልሞች ኦስካር ሳያገኙ መቆየታቸው እንደማያስቆጨው ገልጿል፡፡ ባለፉት ስምንት ዓመታት ለእይታ የበቁት ባለስምንት ክፍል የሃሪፖተር ፊልሞች በመላው ዓለም ከ7 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ከሦስት ሳምንት በኋላ በሚደረገው 84ኛው የኦስካር ሽልማት ሥነስርዓት ላይ የሃሪ ፖተር የመጨረሻ ክፍል የሆነው “ዘ ዴዝሊ ሃሎውስ” ብዙም ግምት በማይሰጣቸው በአርት ዲያሬክሽን፤ በሜክ አፕ እና በቪዥዋል ኢፌክት ዘርፎች በእጩነት ቢቀርብም የማሸነፍ እድሉ ጠባብ እንደሆነ ቢቢሲ ጠቁሟል፡፡የ22 ዓመቱ ዳንኤል ራድክሊፍ እድሜያቸው ከ30 በታች በሆኑ የእንግሊዝ ዝነኞች ባለው 6.1 ቢሊዮን ዶላር ሃብት የመጀመርያ ደረጃ መያዙን ያመለከተው ሰንዴይ ታይምስ፤ ባለፈው አመት ብቻ 51.8 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንደነበረው አውስቷል፡፡ ህ በዚህ እንዳለ በ84ኛው የኦስካር ሽልማት በእጩነት ለሚቀርቡት 150 ተወዳዳሪዎች ልዩ የምሳ ግብዣ መደረጉን ሎስ አንጀለስ ታይምስ ዘግቧል፡፡ በምርጥ ተዋናይነት ጆርጅ ክሉኒና እና ሜሪል ስትሪፕ ሊሸለሙ እንደሚችሉ ከዚሁ የምሳ ግብዣ ጋር ተያይዘው ከወጡ የኦስካር አሸናፊዎች ትንበያ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በኦስካር “ምርጥ ፊልም” ዘርፍ ዘጠኝ ፊልሞች የታጩ ሲሆን በሰሜን አሜሪካ ያስገቡት ገቢ ከአምናው 56 በመቶ መውረዱን ሎስ አንጀለስ ታይምስ አውስቷል፡፡ አምና ለኦስካር ሽልማት በእጩነት የቀረቡት አስር ፊልሞች በሰሜን አሜሪካ 1.234 ቢሊዮን ዶላር ያስገቡ ሲሆን ዘንድሮ ዘጠኝ እጩዎች ያስመዘገቡት 546 ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ ታውቋል፡፡

 

 

 

Read 1096 times Last modified on Saturday, 11 February 2012 09:04