ከሦስት ሳምንት በኋላ በሚደረገው 84ኛው የኦስካር ሽልማት ሥነስርዓት ላይ የሃሪ ፖተር የመጨረሻ ክፍል የሆነው “ዘ ዴዝሊ ሃሎውስ” ብዙም ግምት በማይሰጣቸው በአርት ዲያሬክሽን፤ በሜክ አፕ እና በቪዥዋል ኢፌክት ዘርፎች በእጩነት ቢቀርብም የማሸነፍ እድሉ ጠባብ እንደሆነ ቢቢሲ ጠቁሟል፡፡የ22 ዓመቱ ዳንኤል ራድክሊፍ እድሜያቸው ከ30 በታች በሆኑ የእንግሊዝ ዝነኞች ባለው 6.1 ቢሊዮን ዶላር ሃብት የመጀመርያ ደረጃ መያዙን ያመለከተው ሰንዴይ ታይምስ፤ ባለፈው አመት ብቻ 51.8 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንደነበረው አውስቷል፡፡ ህ በዚህ እንዳለ በ84ኛው የኦስካር ሽልማት በእጩነት ለሚቀርቡት 150 ተወዳዳሪዎች ልዩ የምሳ ግብዣ መደረጉን ሎስ አንጀለስ ታይምስ ዘግቧል፡፡ በምርጥ ተዋናይነት ጆርጅ ክሉኒና እና ሜሪል ስትሪፕ ሊሸለሙ እንደሚችሉ ከዚሁ የምሳ ግብዣ ጋር ተያይዘው ከወጡ የኦስካር አሸናፊዎች ትንበያ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በኦስካር “ምርጥ ፊልም” ዘርፍ ዘጠኝ ፊልሞች የታጩ ሲሆን በሰሜን አሜሪካ ያስገቡት ገቢ ከአምናው 56 በመቶ መውረዱን ሎስ አንጀለስ ታይምስ አውስቷል፡፡ አምና ለኦስካር ሽልማት በእጩነት የቀረቡት አስር ፊልሞች በሰሜን አሜሪካ 1.234 ቢሊዮን ዶላር ያስገቡ ሲሆን ዘንድሮ ዘጠኝ እጩዎች ያስመዘገቡት 546 ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ ታውቋል፡፡