Saturday, 11 February 2012 09:04

በታዳጊ ተዋናዮች የተሰራው ‹ክሮኒክል› ገበያውን ይመራል

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(1 Vote)

ብዙም በማይታወቁ ታዳጊ ተዋናዮች የተሰራው “ዘ ክሮኒክል” ባለፈው ሳምንት ተመርቆ ለዕይታ የቀረበ ሲሆን በሰሜን አሜሪካ 22 ሚሊዮን ዶላር በማስገባት የቦክስ ኦፊስን ደረጃ እየመራ እንደሚገኝ ዘ ሆሊውድ ሪፖርተር ዘገበ፡፡ በ”ትዌንቲ ሴንቸሪ ፎክስ” 60 ሚሊዮን ዶላር ወጥቶበት የተሰራው ፊልሙ፤ በላቀ ልዩ ችሎታው የተነሳ ችግር ውስጥ በሚገባ ታዳጊ ህይወት ዙርያ ያጠነጥናል፡፡ “ዘ ክሮኒክል” ከሰሜን አሜሪካ ውጭ በ33 ቦታዎች ለተመልካች በመቅረቡ ተጨማሪ 15 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቱን የጠቀሰው ዘ ሆሊውድ ሪፖርተር፤ የመላው ዓለም አጠቃላይ ገቢው 35 ሚሊዮን ዶላር እንደሆነም አመልክቷል፡፡ በ ”ሃሪፖተር” ስምንት ክፍል ፊልሞች የተወነው ዳንኤል ራድክሊፍ የሚሰራበት “ዉመን ኢን ብላክ” በ21 ሚሊዮን  ዶላር ገቢ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

 

 

Read 1132 times Last modified on Saturday, 11 February 2012 09:06