Saturday, 11 February 2012 09:06

የሆሊውድ ውሾች ይሸለማሉ

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

በሆሊውድ ለሚሰሩ ውሾች የመጀመርያው የኮከብ ትወና ሽልማት “ጎልደን ኮላር” ሊሰጥ ነው፡፡  ለውሾቹ ወርቃማ የአንገት ማሰርያየሚሸልመውስነስርዓቱ የፊታችን ሰኞ በሎስአንጀለስ ይካሄዳል፡፡ ዎልስትሪት ጆርናል እንደዘገበው፤ በሆሊውድ መንደርውሾችበትወናሙያላለፉት50ዓመታት ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን አንዳንድ ፊልሞች ከመሪ ተዋናዮቹ ይልቅ በውሾቹ አስደናቂ የትወና ብቃትና አማላይ ገፀባህርይ ገቢያቸው እንደሚሟሟቅ ይነገራል፡፡

ለመጀመርያው የጎልደን ኮላር ሽልማት በ”ዘ አርቲስት” ፊልም ላይ ያለችው ‹ሃውጊ› የተባለች ድንክ ውሻና በማርቲን ስኮርሲስ ፊልም ‹ሁጎ› ላይ ያለው ሶሎግ ውሻ ‹ብላኪ› ዋና ተፎካካሪዎች ሆነዋል፡፡ በሆሊውድ በሚሊዮን ዶላር የሚሰላ ገቢ ያላቸው በርካታ የውሾች ዝርያዎች መኖራቸውን የሚያትተው ዎልስትሪት፤ ይሁንና ውሾቹ ከእንስሳነት ባህርያቸው ይልቅ ሰዋዊ ስብእና እንዲተውኑ እየተደረጉ ጫና ውስጥ እንደሚገቡ ዘግቧል፡፡ ውሾች ከተወኑባቸው የቅርብ ጊዜ ፊልሞች “ቢግነርስ” እና “ያንግ አደልት” ይጠቀሳሉ፡፡

 

 

 

Read 1125 times Last modified on Saturday, 11 February 2012 09:11