Print this page
Saturday, 11 February 2012 09:12

ማዶና በሙዚቃዋ ዓለምን ልትዞር ነው

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ ፊልም ዲሬክተርነት የገባችው የፖፕ ሙዚቃ ንግስት ማዶና እስከሚቀጥለው ዓመት የሚዘልቅ “ስቲክ ኤንድ ስዊት” የተሰኘ ኮንሰርት በመላው ዓለም ልታቀርብ እንደሆነ ተገለፀ፡፡ በሰሜን አሜሪካ 26፣ በአውሮፓ 26 ከተሞችን የምታዳርሰው የ50 ዓመቷ ማዶና፤ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ አውስትራልያ እንደምትጓዝ ቢልቦርድ ጠቁሟል፡፡ ሰሞኑን አርቲስቷ በአሜሪካው ታላቅ የስፖርት ውድድር “ሱፐር ቦውል” ላይ ያቀነቀነች ሲሆን 114 ሚሊዮን ተመልካች እንደታደመው የጠቀሰው ኤምቲቪ፣ በሱፐር ቦሉ ግጥሚያ ግን 3 ሚሊዮን ተመልካች ብቻ እንደተገኘ አውስቷል፡፡

ማዶና እስከ 2013 የሚዘልቀውን ዓለም አቀፍ ኮንሰርት ስታጠናቅቅ “ኤምዲኤንኤ” የተባለ አዲስ አልበም እንደምታወጣ ኤምቲቪ ዘግቧል፡፡ ከ2002 ወዲህ በየዓመቱ 50 ሚሊዮን ዶላር አማካይ ገቢእያገኘች ያለችውአርቲስቷ፤በሙዚቃብቻሳይሆንበፊልምዲያሬክቲንግምስኬታማእየሆነችመምጣቱዋን ያመለከተው ኤምቲቪ፤ “የማታረጅ ኮከብ” ብሏታል - ማዶናን፡፡ አርቲስቷ በ2009 ባቀረበችው ኮንሰርት 400 ሚሊዮን ታዳሚ በማግኘት 1.2 ቢሊዮን ዶላር እንደሰራች ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

 

 

Read 1460 times Last modified on Saturday, 11 February 2012 09:14