በህንዳዊው አቀንቃኝ በዲፒ ሼንዲ ተደርሶ የተዘጋጀው “ወፍራም ዱርዬ” የተሰኘ ፊልም የፊታችን ሠኞ በ11 ሠዓት በእምቢልታ ሲኒማ እንደሚመረቅ ተገለፀ፡፡ በፊልሙ ላይ አርቲስት ሳምሶን ታደሠ/ቤቢ/፣ እፀህይወት አበበ፣ ሸዋፈራሁ ደሳለኝ፣ ፋንቱ ማንዶዬ እና ሌሎች የሚሳተፉበት ሲሆን ፊልሙን ሠርቶ ለማጠናቀቅ አንድ አመት እንደፈጀ ታውቋል፡፡ ፊልሙ አንድ ሚሊዮን ብር እንደወጣበት አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡