Saturday, 11 February 2012 09:18

STRANGE” የስዕል አውደ ርዕይ ማክሰኞ ይከፈታል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

በሰዓሊ ሮቤል ብርሃኔ የተዘጋጁ 50 ስዕሎች የሚቀርቡበት “STRANGE” የስዕል አውደ ርዕይ በመጪው ማክሰኞ አምስት ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዘክር ተመርቆ ይከፈታል፡፡ 50ዎቹ አክሌሪክ ስዕሎች የሰዓሊው የአንድ አመት ሥራዎች ናቸው፡፡ ሮቤል ለብቻው አውደ ርዕይ ሲያዘጋጅ ይህ ሦስተኛው ሲሆን በጋራ ከ20 ጊዜ በላይ አቅርቧል፡፡ ሰዓሊው አምና የአሜሪካ ኤምባሲ ባዘጋጀው “ዘ ፎር ፍሪደም” ስዕል አሸናፊ በመሆን 25ሺህ ብር የተሸለመ ሲሆን ሌሎች በርካታ ሽልማቶች እንዳሉትም ማወቅ ተችሏል፡፡ይህ በዚህ እንዳለ የሜክሲኮ ኤምባሲ ያዘጋጀው የስዕል አውደ ርዕይ ባለፈው ረቡዕ  ከአሊያንስ ኢትዮ ፍራንስ ጋር በመተባበር ተከፈተ፡፡ እስከ የካቲት 20 የሚቆየው “Signs of History” በተሰኘው አውደ ርዕይ ማርታ ዴልጋዶ እና ካሳንድራ ሳባክ ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡

 

 

Read 1021 times Last modified on Saturday, 11 February 2012 09:21