Saturday, 11 February 2012 09:21

“ዴርቶጋዳ” ወደ እንግሊዝኛ ተተረጐመ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(1 Vote)

በደራሲ ይስማዕከ ወርቁ ተፅፎ ለንባብ የበቃው “ዴርቶጋዳ” ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉሞ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ለንባብ በቃ፡፡ ዘላለም ንጉሤ የተረጎመውን መፅሐፍ ያሳተመው ዩኒቲ ፐብሊሸርስ ሲሆን መፅሐፉ በፋር ኢስት ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግል ማህበር ነው የታተመው፡፡ በመፅሐፉ ጀርባ ላይ ዶ/ር ታዬ አሰፋ፣ ደራሲና ሃያሲ መስፍን ሃብተማርያም፣ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ እና ካፒታል የእንግሊዝኛ ጋዜጣ አስተያየት አስፍረዋል፡፡ በሀገር ውስጥ በ 74.99 ብር፣ በውጭ ሀገራት 12.99 ዶላር ለገበያ የቀረበው ባለ 358 ገፅ መፅሐፍ በመጪው ሳምንት እንደሚመረቅ ታውቋል፡፡

 

 

Read 3640 times Last modified on Saturday, 11 February 2012 09:24