Saturday, 11 February 2012 09:25

ፖየቲክ ጃዝ” ረቡዕ ይቀርባል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

ወጣት ገጣሚያንና የሙዚቃ ባለሙያዎች የተቀናጁበት ወርሃዊ የኪነጥበብ ዝግጅት በመጪው ረቡዕ ምሽት 12፡30 በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ይቀርባል፡፡ ገጣሚና ተዋናይ ሜሮን ጌትነት መድረክ በምትመራበት ዝግጅት ረዳት ፕሮፌሰር ኃይማኖት አለሙ ከ“ቴዎድሮስ” ትያትር ቅንጭብ የሚያቀርብ ሲሆን፣ አርቲስት ታምሩ ብርሃኑ መነባንብ፣ አባባው መላኩ፣ በረከት በላይነህ፣ ቸርነት ወልደገብርኤል፣ ምልዕቲ ኪሮስና ሌሎችም የግጥም ሥራዎቻቸውን ከመለከት ባንድ የጃዝ ሙዚቃዎች ጋር በማጣመር ያቀርባሉ፡፡ የመግቢያ ዋጋውም 50 ብር እንደሆነ ማወቅ ተችሏል፡፡

 

 

Read 1061 times Last modified on Saturday, 11 February 2012 09:28