(አሜሪካዊ አክተርና ኮሜዲያን - ስለ ሬጋን አስተዳደር የተናገረው)
ስላቅን አለመፃፍ አስቸጋሪ ነው፡፡
ጁቬናል
(የሮማ ገጣሚ)
ሬዲዮ ማዳመጥ ከተውኩኝ በኋላ አስፕሪን ከመግዛት ባተረፍኩት ገንዘብ መኖር ችያለሁ፡፡
ፍሬድ አሌን
(አሜሪካዊ ኮሜዲያን)
ጦር ሠራዊቱን የማትጠቀምበት ከሆነ ለጥቂት ጊዜ ልዋስህ እወዳለሁ፡፡
አብርሃም ሊንከን
(የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩ - በአሜሪካ የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት የጀነራል ጆርጅ ቢ. ማክሌላን ያለ ወታደራዊ እንቅስቃሴ መቀመጥ አናዷቸው ከፃፉት ደብዳቤ የተወሰደ)
ኮሜዲ ለመስራት የሚያስፈልጉኝ:- መናፈሻ፣ ፖሊስና ቆንጆ ኮረዳ ብቻ ናቸው፡
ቻርሊ ቻፕሊን
(የብሪቲሽ አክተርና ዲሬክተር)
የእንግሊዝ ተመልካቾች ፊት መቅረብ ያስደስተኛል፡፡ መሳቅ ባያሰኛቸው እንኳን እንደገባቸው ለማሳየት ጭንቅላታቸውን ይነቀንቃሉ፡፡
ቦብ ሆፕ
(ትውልደ - ብሪቲሽ አሜሪካዊ ኮሜዲያንና
የፊልም ተዋናይ)
ኮሜዲ መድሃኒት ነው፡፡
ትሬቨር ግሪፊትዝ
(የብሪቲሽ ፀሐፌ ተውኔት)
የሰውን ልጅ ጅልነትና ክፋት ማሳየት የኮሚክ ገጣሚ ሥራ ነው፡፡
ዊሊያም ኮንግሪቭ
(እንግሊዛዊ ፀሐፌ ተውኔትና ገጣሚ)
ጣቴን ብቆርጥ ትራጄዲ ነው፡፡ ክፍት የውሃ መውረጃ ቱቦ ውስጥ ገብቼ ብሞት ግን ኮሜዲ ነው፡፡
ሜል ብሩክስ
(አሜሪካዊ የፊልም አክተርና ዲሬክተር)