መሳም እወዳለሁ፡፡ የሥራዬ አካል ነው፡፡ እግዚአብሔር ወደዚህ የላከኝ ብዙ ሰዎችን ለመሳም ነው፡፡
ኬሪ ፊሸር
(አሜሪካዊ ተዋናይና ፀሐፊ)
ከብቶች ወደ በረታቸው እስኪገቡ ድረስ ሳም፡፡
ቤውሞንት እና ፍሌትቸር
(እንግሊዛዊ ፀሐፌ ተውኔት)
መሳም ቀድሞ ይመጣል፤ በኋላ እርግማን ይከተላል፡፡
የሜክሲኮአዊያን አባባል
እሱ ሳመኝ፤ እናም አሁን ሌላ ሰው ሆኛለሁ፡፡
ጋብሬላ ሚስትራል
(ስፓኒሽ ገጣሚ፣ ዲፕሎማት እና የትምህርት ባለሙያ)
የወንደላጤ ቀለብ:- ዳቦና አይብ እና ስሞሽ፡፡
ጆናታን ስዊፍት
(አንግሎ - አይሪሽ ፀሐፊና ቄስ)