(ስለ ዳንስ)
- በዳንስ ወለል ላይ አሸርን የምረታው ይመስለኛል፡፡
ክሪስ ብራውን
- ከስድስት ወንድሞቼ ጋርነው ያደግሁት፡፡ ዳንስን የተማርኩት እንደዚያ ነው - የመታጠቢያ ቤት ወረፋ እየጠበቅሁ፡፡
ቦብ ሆፕ
- ከፍሰቱ ጋር እፈሳለሁ፡፡ ለእኔ ምንም ዓይነት ሙዚቃ ብታጫውቱልኝ እደንሳለሁ፡፡
ጋኤል ጋርሽያ ቤርናል
- ዕልድ የዳንስ ወለሉ ላይ ከወጡት ጋር ትደንሳለች፡፡
ኤች. ጃክሰን በራውን ጄአር
- ዛሬ ህፃናቱ በፊታቸው መደነስ የሚች የመስላቸዋል፡፡
ጓንገር ሮጀርስ
- ጀስቲን ቢበር የፀጉር ቁርጤን ሰረቀኝ፡፡ አክል ሮዝ ደግሞ ዳንሴን!
ዴቪ ጆንስ
- ዴኒስ ሎው በእንቁላል ቅርፎቶች ላይ መደነስ ይችላል፡፡
ቢል ሸንክሊ
- የምትኖረው መደነስ እስከቻልክ ድረስ ነው፡፡
ሩዶልፍ ኑሩዬቭ
- በደብን መደነስ ባትችል ማንም ደንታ የሚሰጠው የለም፡፡ ዝም ብለህ ተነስተህ ደንስ፡፡
ዴቭ ባሪ
- ሚስቶች፤ በበቂ ሁኔታ ደንሰናል ብለው የማያስቡ ሰዎ ናቸው፡፡
ግሮሾ ማርክስ
- መዝፈን፣ መደነስ ወይም መተወን አልችልም፤ የቶክ ሾው አዘጋ ከመሆን ውጭ ሌላ ምን ልሆን እችል ነበር፡፡
ዴቪድ ሌተርማን
- ሰዎች ውበትን ለማየት ይመጣሉ፤ እኔም የሚሹትን ለመስጠት እደንሳለሁ፡፡
ጁዲት ጃሚሶን
- ዳንስ ስህተት አልባ እቅጩነት ሊኖረው ይገባል፡፡
አሪሌ ዶምባስሌ
Published in
የግጥም ጥግ