Print this page
Saturday, 18 February 2012 10:51

“በሃይማኖት ሽፋን… አስከ መቼ?” ተመረቀ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

በወይዘሮ እጅጋየሁ በየነ የተዘጋጀውና በአቡነ ጳውሎስ ሕይወት ታሪክ ላይ ያተኮረው “በሃይማኖት ሽፋን… እስከ መቼ?” ባለ 103 ገፅ መፅሐፍ ከትናንት ወዲያ ማምሻውን ፓትርያርኩ ባልተገኙበት በሂልተን ተመረቀ፡፡ መፅሐፉ ከያዛቸው አርእስቶች መካከል የፓትርያርኩን አለም አቀፍ አገልግሎት ጵጵስና እሃ ስደት፣ ፓትርያክነት እና ለአቡነ ጳውሎስ ሃውልት ስለማቆም የተወሱ አርእስቶችን ይዟል፡፡ በቦሌ ደብረ ሰላም መድሃኔዓለም ደብር ሠራ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ደራሲዋ በአቡነ ጳውሎስ ሃውልት ግንባታም ጉልህ ድርሻ እንደነበራቸው ይነገራል፡፡ ምንም አይነት ማጣቀሻ በማጣቀሻ ገፁ ያልተካተተበት መፅሐፍ በ20 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡ በምርቃቱ ጊዜ ንግግር ያደረጉት ወይዘሮ እጅጋየሁ “እውነታውን ለማሳወቅ ብዬ ፅፌዋለሁ፡፡

ብሮሹር ነው ብዬ ነበር፤ አባቶች ከ50 ገፅ ከበለጠ መፅሐፍ ነው አትስጊ ብለውኛል፡፡ አንድም ውሸት ስላልፃፍኩ ማንንም ይቅርታ አልጠይቅም” ብለዋል፡፡ በምረቃው ወቅት የታውን ባለ 10 ደቂቃ “ዶክመንታሪ” ፊልምም የእለቱ መራኼ መድረክ እጅጋየሁ ስለ ፓትርያርኩ ለመፃፍ ተገቢ መሆናቸውን ተናግሯል፡፡ ወ/ሮ እጅጋየሁ የመፅሐፉን ማስታወሻነት ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ወላጆች ለአፈመምህር ገብረዮሐንስ ገብረሥላሴ እና ለወይዘሮ አራደች ተድላ አበርክተዋል፡

 

 

 

Read 1110 times Last modified on Saturday, 18 February 2012 10:53