Saturday, 06 February 2016 11:17

በ13ኛው “ቅድሚያ ለሴቶች” ከ40 ክለቦች 314 አትሌቶች ይሳተፋሉ

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(1 Vote)


             የጤና ሯጮችም 10ሺ ናቸው
    ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለ13ኛው “ቅድሚያ ለሴቶች” የ5 ኪሎ ሜትር የጐዳና ላይ ሩጫ ምዝገባውን ሰኞ እንደሚጀመር አስታወቀ፡፡ የጎዳና ላይ  ሩጫው በየዓመቱ ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን ምክንያት በማድረግ በዋዜማው ሰሞን ሲታወቅ  ላለፉት 12 ዓመታት በተከታታይ በስኬት ተካሂዷል።
ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን ዘንድሮ የሚከበረው ለ40ኛ ጊዜ ሲሆን ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በጎዳና ላይ ሩጫው ያነገበው መርህ “ለፆታ እኩልነት በጋራ እንቁም” የሚል ይሆናል፡፡
በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስር ከሚገኙ 40 ክለቦች 314 አትሌቶች በጐዳና ላይ ሩጫው እንደሚሳተፉ ይጠብቃል ያሉት አዘጋጆቹ፤ እያንዳንዱ ክለብ በአማካይ 3 አትሌቶችን እንደሚያወዳድርም  ገልፀዋል፡፡
በጐዳና ላይ ሩጫው ለ1ኛ 15ሺ ብር፤ ለ2ኛ 7500 ብር እንዲሁም ለ3ኛ 5ሺ የገንዘብ ሽልማት እንደሚኖርም ታውቋል። በ5ኪሎ ሜትር ጐዳና ላይ ሩጫው ከ10ሺ በላይ የጤና ሯጮች እንደሚካፈሉበትም ይጠብቃል፡፡

Read 3332 times