Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 18 February 2012 10:55

የፖለቲካ ጥግ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ሥልጣን ሁልጊዜም በተጠያቂነት ሚዛኑን እንዲጠብቅ መደረግ አለበት፡፡ ያለዚያ ጨቋኝ ነው የሚሆነው፡፡

ፒተር ድሩከር

(ትውልደ - ኦስትሪያ አሜሪካዊ

የማኔጅመንት አማካሪ)

ያ ወሬኛ መነኩሴ!

ቤኒቶ ሙሶሎኒ

(የጣሊያን አምባገነን መሪ የነበረ - አዶልፍ ሂትለርን በተመለከተ የተናገረው)

የኮሙኒስት ፓርቲ አምባገነንነት የሚጠበቀው ማንኛውንም የሃይል አማራጭ በመጠቀም ነው፡፡

 

 

ሊኦን ትሮትስኪ

(ሩሲያዊ አብዮታዊ መሪ)

እናንተ ምርጫውን ብታሸንፉም እኔ ደግሞ ቆጠራውን አሸንፌአለሁ፡፡

አናስታስዮ ሶሞዛ ዲባይሌ

(የኒካራጉዋ አምባገነን መሪ የምርጫ ኮረጆ ተጭበርብሯል ለሚለው ውንጀላ የሰጡት ምላሽ)

የግብረገባዊም ሆነ የመንፈሳዊ ህይወቴ አወቃቀር አምባገነን እንድሆን አይፈቅድልኝም፡፡ አምባገነን ብሆን ኖሮ ብዙ ነገሮች ሊከሰቱ ይችሉ ነበር፡፡

አውጉስቶ ፒኖቼት

(የቺሊ ወታደራዊ አምባገነን)

ወደ ሰማይ መብረር፤ ምድርን ሰንጥቀን መግባት እንችላለን፡፡ ምክንያቱም ታላቁ መሪያችን ሊቀመንበር ማኦ ከፍተኛው አዛዣችን ናቸው፡፡

ማንነቱ ያልታወቀ

በማንኛውም አገር የሚሞቱ ሰዎች መኖር አለባቸው፡፡ የትኛውም ህዝብ ህግና ስርዓት ለማስከበር የሚከፍላቸው መስዋእት ናቸው፡፡

ኢዲ አሚን

(የኡጋንዳ አምባገነን መሪ የነበሩ)

ህዝቤና እኔ ሁለታችንንም የሚያረካ ስምምነት ላይ ደርሰናል፡፡ እነሱ ያሰኛቸውን እንዲናገሩ፤ እኔም ያሰኘኝን እንዳደርግ፡፡

ዳግማዊ ፍሬድሪክ

(የፕሪሽያ ንጉስ የነበሩ)

ይሄ ስራ እኔ ፈልጌው ያገኘሁት ሳይሆን እጣ ፈንታ የሰጠኝ ነው፡፡

አውጉስቶ ፒኖቼት

(የቺሊ ወታደራዊ አምባገነን መሪ የነበሩ)

የሰው ልጅ የአዕምሮ እድገት ላይ ወሰን የሚያደርግ የሂትለርንም ሆነ የማንኛውንም መንግስት ውሳኔ እቃወማለሁ፡፡

ኧርነስት ቤቪን

(የብሪቲሽ ሌበር ፓርቲ መሪና

ከፍተኛ የፖለቲካ ሹም)

 

 

 

Read 3601 times Last modified on Saturday, 18 February 2012 10:58