Saturday, 06 February 2016 11:29

“ሕያው ጥበብ፤ አላፊ ሕይወት” የሥዕል ትርኢት ይከፈታል”

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

     የጋለሪያ ቶሞካ 19ኛው ዙር የሥዕል ትርኢት “ሕያው ጥበብ፤ አላፊ ሕይወት” በሚል ርዕስ የፊታችን አርብ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ሳር ቤት ካናዳ ኤምባሲ ፊት ለፊት በሚገኘው ቤተ - ሥዕል እንደሚከፈት የጋለሪው አርት ዳይሬክትር ሰዓሊ እሸቱ ጥሩነህ ገለፁ፡፡
በትርኢቱ በህይወት የሌለው የሰዓሊ ኤርሚያስ ማዘንጊያ ከ35 በላይ ስዕሎች ለእይታ የሚቀርቡ ሲሆን በሰዓሊው እህት ትዕይንት ማዘንጊያ ጠያቂነትና በጋለሪያ ቶሞካ ተባባሪነት ለእይታ አውደ ርዕዩ እንደተዘጋጀ ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ የሥዕል ትርኢቱ ለቀጣዮቹ ሁለት ወራት ለእይታ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በተከፈተ በወሩ በስዕሎቹ ላይ ውይይት እንደሚካሄድባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 2451 times