Saturday, 20 February 2016 10:11

ገንዘቤ ከ31ኛው ኦሎምፒያድ በፊት እያንፀባረቀች ነው

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

      በዓለም  የአትሌቲክስ  ስፖርት  በኢትዮጵያውያን አትሌቶች  የዓለም ሪከርዶች የሚሰበሩበት እድል እየተመናመነ ቢመጣም  በመካከለኛ ርቀት ግን የገንዘቤ ዲባባ የበላይነት እንደቀጠለ ነው፡፡   በሴቶች መካከለኛ ርቀት የቤት ውስጥ እና የትራክ ውድድሮች በገንዘቤ ዲባባ ቁጥጥር ስር ያሉት ክብረወሰኖች 4 ደርሰዋል፡፡ በአይ.ኤ.ኤ.ኤፍ የ2015 የዓለም ኮከብ አትሌት ሆና የተመረጠችው ገንዘቤ ዲባባ ሪኮርዶች እየቀሩ ባሉበት የአትሌቲክስ የስፖርት መድረክ በየዓመቱ አዳዲስ ክብረወሰኖች እያሻሻለች መቀጠሏ ከፍተኛ አድናቆት እያስገኘላት ነው፡፡ በተለይ በፌብርዋሪ ወር ላይ በአውሮፓ በምታደርጋቸው ውድድሮች ሪከርዶቿን በሙሉ ለማስመዝገብ በቅታለች፡፡ በሪዮ ዲጄነሮ ከስድስት ወራት በኋላ በሚደረገው 31ኛውኦሎምፒያድ ምናልባትም የመጀመርያ የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያዋን እንደምታገኝ ተገምቶላታል፡፡ ገንዘቤ አሁን በቁጥጥሯ ስር የሚገኙት 4 ሪከርዶች፤ የዓለም ፤የአፍሪካ እና  የኢትዮጰያ ክብረወሰኖች ናቸው፡፡ ገንዘቤ ባለፉት ሁለት ዓመታት ያስመዘገበቻቸው ክብረወሰኖች ከ10 እና ከ20 ዓመታት በላይ ሳይሰበሩ የቆዩ በመሆናቸው የአትሌቷን የላቀ ብቃት የሚያመለክቱ ናቸው፡፡  ሰሞኑን ያስመዘገበችው የ1 ማይል ክብረወሰን ለ26 ዓመታት እንዲሁም ባለፈው የውድድር ዘመን ያስመዘገበችው የ1500 ሜትር ክብረወሰን ለ22 ዓመታት ሳይሰበሩ የቆዩ ናቸው፡፡ ገንዘቤ በኦልአትሌቲክስ ዶት ኮም ወቅታዊ የእተሌቶች የብቃት ደረጃ መሰረት በሁሉም ውድድሮች በ1461  ነጥብ ከዓለም አንደኛ ደረጃ ይዛ ትገኛለች፡፡

Read 1958 times