Saturday, 27 February 2016 12:30

“ ... በአለም... 303.000/እናቶች በየአመቱ ይሞታሉ...”

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

ከ2015-2030/ የእናቶች ሞት ከ1000/በሕይወት ከሚወለዱ 70/እንዲሆን አለም አቀፍ ስምምነት ተደርሶአል፡፡

    የኢትዮያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር 24ተኛውን አመታዊ ጉባኤ በውጭው አቆጣጠር ፌብረዋሪ 16 እና 17/20016/ ማለትም የካቲት 8/እና 9/2008 ዓ/ም በአዲስ አበባ ሒልተን ሆል አካሂዶአል፡፡ የጉባኤው መሪ ቃልም ከምእተ አመቱ የልማት ግብ ወደ ዘለቄታዊ የልማት ግብ በሚደረገው ሽግግር የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ሊያደርግ የሚገባውን አስተዋጽኦ የሚመለከት ነው፡፡ በስብሰባው ላይ ወደ 200/ የሚሆኑ የማህበሩ አባላት የተገኙ ሲሆን በተጨማሪም ተባባሪ አባላት እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተው ነበር፡፡ የኢሶግ 24ኛው ጉባኤ የክብር እንግዳ ዶ/ር ከበደ ወርቁ የኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስር ሚኒስትር ደኤታ ነበሩ፡፡ ዶር ከበደ ወርቁ የኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስር ሚኒስትር ደኤታ በጉባኤው መክፈቻ ላይ የሚከተለውን ንግግር አድርገዋል፡፡
“ ... የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር  ESOG 24ኛ አመታዊ ጉባኤ በማህበሩ አባላትና ሌሎች በስብሰባው ላይ የተገኙ የጤናው ዘርፍ አባላት መካከል ለውይይትና ተመሳሳይ ግንዛቤ እንዲፈጠር የሚረዱ ነጥቦች እንደሚቀርቡ እምነ ነው፡፡ በኮንፍረንሱ ለውይይት የሚቀርቡት ሳይንሳዊ ምርምሮች እና በተለይም ከምእተ አመቱ የልማት ግብ ወደ ዘለቄታው የልማት ግብ መሸጋገርን በሚመለከት ጉባኤው የአገልግሎቱን በጥራት እና በብቃት መቀጠል ግቡ አድርጎ የሚነጋገርባቸው ነጥቦች ከስነተዋልዶ ጤና አኩዋያ ስንመዝነው እጅግ ጠቃሚ ናቸው፡፡
በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ለ2ኛ ጊዜ በታቀደው የእድገትና የልማት እቅድ ቀጣይነት ያለው የልማት ግብን በተሸሻለና ባደገ መልኩ እንዲተገበር ስራ ተጀምሮአል፡፡ አለም ቀጣይነት ያለው የልማት ግብን እውን ለማድረግ 17/ ግቦችና 169/ የስራ አቅጣጫዎች በመንደፍ በቀጣዮቹ 15/ አመታት ተግባራዊ ለማድረግ የተስማማች ሲሆን ኢትዮጵያም የዚሁ አካል ነች፡፡ ዘለቄታዊ የልማት ግቡን ከምእተ አመቱ የልማት ግብ የሚለየው ድህነትን ከስር መሰረቱ ምንጩን ለማድረቅ ስራ መሰራት እንዳለበት በማስቀመጡ ሲሆን ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ይጠበቃል፡፡ በቀጣይ የልማት ግቡ ተራ ቁጥር 3.1/ እና 3.2/ የእናቶችን ሞት መቀነስና የጨቅላዎችና ከአምስት አመት በታች ያሉ ሕጻናት ለሞት የሚዳረጉበትን ምክንያት ማስወገድ  እንደሚገባ ተጠቅሶአል፡፡ ኢትዮጵያ የምእተ አመቱ ግብ ካስቀመጠው ጊዜ አስቀድማ የህጻናትን ሞት በመቀነስ ረገድ ከአፍሪካ  ጥቂት አገራት መካከል የምትገኛ ሲሆን የእናቶች ሞት መጠንም በ73/ በመቶ በመቀነሱ ከፍተኛ ርብርብ የተደረገበት መሆኑን ያሳያል፡፡ ይህንን ግብ ለማግኘትም ኢትዮጵያ ጠንካራና መልካም አስተዳደርን በመፍጠር እንዲሁም የህክምና አገልግሎቱን ቀድሞ ከነበረው በተሻለ ተደራሽ በማድረግ ብዙ ስራ ሰርታለች፡፡
የህክምና አገልግሎቱ ይበልጡኑ እንዲደራጅና ባለሙያዎችም በተሻለ አሰራር ሕብረተሰቡን እንዲያገለግሉ ለማድረግ እንደ የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ያሉ የሙያ ማህበራት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ቀላል አይደለም፡፡ ቀጣይነት ያለውን የልማት ግብ እውን ለማድረግም ጠንካራ ድጋፍ እና ትብብር የሚያስፈልግ ሲሆን የኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስ ርም እንደመሑሀ ካሉ የሙያ ማህበራት ጋር ያለውን ግንኙነት አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ከሁለት አስርት አመታት በላይ ከኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስር ጋር በመተባበር የሰራ ሲሆን ስራውም ከፖሊሲና ከተግባራዊ እንቅስቃሴ ጋር የተጣመረ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ስለዚህም የኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስር በቀጣዮቹ አመታትም ከኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበርጋር በመተባበር ቀጣይነት ያለውን የልማት ግብ እውን ለማድረግ ይጥራል፡፡”  ብለዋል፡፡
    ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት የአለም አቀፉ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ፌደሬሽን የቦርድ አባልና የአፍሪካ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ፕሬዝደንት በኮንፍረንሱ ወቅት ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት መልስ የሚከተለው ነው፡፡
“ ... የ2015/ ዳታ እንደሚያሳየው በአለም ላይ 303.000/እናቶች በየአመቱ የሚሞቱ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 1000/አንድ ሺህ ብቻ በሰለጠኑት አገራት ይሞታሉ፡፡ ቀሪዎቹ የሚሞቱት በማደግ ላይ ባሉ አገራት ውስጥ ነው፡፡ ከዚህም 2/3ኛ የሚሆኑት እናቶች የሚሞቱት ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት ነው፡፡ ይህ በአለም ላይ የሚታወቅ እውነታ ሲሆን እናቶቹ የሚሞቱትም በምን ምክንያት እንደሆነ እውቅ ነው፡፡ በህመምተኛዋ ወይንም በቤተሰብ ቸልተኝነት፣ አቅም በማጣት ወይንም ዘግይቶ ወደ ጤና ተቋም በመድረስ ፣አለዚያም አንዳንድ ሁኔታዎች ባለመሙዋላታ ቸው ሊሆን ይችላል፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ሁኔታ ስንመለስ የእናቶችን ሞት በሚመለከት በእርግጥ ሞትን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የማይቻል ቢሆንም ነገር ግን ባለፉት 20/አመታት ውስጥ ከፍተኛ ለውጥ አለ፡፡ ለምሳሌም ከሀያ አመታት በፊት ከ100.000/በሕይወት ከሚወለዱ ሕጻናት ውስጥ ከ1000/በላይ እናቶች ይሞቱ የነበረ ሲሆን በ2015/የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ በፊት ከነበረው የሞት መጠን በ73/በመቶ ቀንሳለች፡፡ የምእተ አመቱ ግብ የነበረው 75/ከመቶ መቀነስ ሲሆን 73/ከመቶ መቀነስ ማለት እጅግ ተቀራራቢ የሆነ ውጤት መሆኑ እሙን ነው፡፡  የጤና አገልግሎቱን ተደራሽነትም ስናይ ከሀያ አመት በፊት ከግማሽ በታች የሚሆነው ሕዝብ ተጠቃሚ የነበረ ሲሆን አሁን ግን 95/በመቶ የሚሆነው ሕዝብ የጤና አገልግሎቱን ሊያገኝ የሚችልባቸው ሁኔታዎች ተመቻችተዋል፡፡ የህክምና ተቋማቱ ቁጥር መጨመር፣ የህክምና አገልግሎት አሰጣጡ መሻሻል ፣የባለሙያዎች ቁጥር መጨመር እን ዲሁም በገጠሩ ሕዝብ ዘንድ ያለው የጤና አደረጃጀት መሻሻል የእናቶችን ሞት ከመቀነስ እና የጨቅላ እና ከአምስት አመት በታች ያሉ ሕጻናትን ሞት በመቀነስ ደረጃ ከፍተኛ ስራ የተሰራ መሆኑን ያመላክታል፡፡ ስለዚህ በኢትዮጵያ በስነተዋልዶ ጤናም ይሁን በሌሎች የህክምና ዘርፎች አገልግሎቱ ከፍተኛ ለውጥ የተመዘገበበት መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በከፍተኛ ደረጃ ለው ጦች ከታዩባ ቸው አገራት ውስጥም ኢትዮጵያ የተካተተች ነች፡፡ በእርግጥ እድገት የማያቋርጥ ነገር በመሆኑ መሻሻል ያለባቸው ነገሮች እንደሚኖሩ አይካድም፡፡ከ2015-2030 ድረስ በአለም ላይ ያለውን የእናቶች ሞት ከመቶ ሺህ በሕይወት ከሚወለዱ ሕጻናት የእናቶች ሞት ቁጥር 70/እንዲሆን አለም ተስማምቶአል፡፡ ነገር ግን በጣም ጠንክረን ብንሰራ እንዲያውም ወደ 50/ ገደማ እንደርሳለን የሚል እምነት አለ፡፡ “  ሲሉ ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት አስረድተዋል፡፡  
    ዶ/ር ደረጀ ንጉሴ የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት እና የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ፕሬዝዳንት  ኮንፍረንሱ በተካሄደበት ወቅት ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተው ነበር፡፡
“ ...  የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ላለፉት 24/አመታት ለእናቶች እና ጨቅላ ሕጻናት እንዲሁም ባጠቃላይ የስነተዋልዶ ጤና አገልግሎትን በመስጠትና ተገቢውን እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቶአል፡፡ በዚህ አመት በተደረገው አመታዊ ጉባኤ በተለይም የምእተ አመቱን የል ማት ግብ መጠናቀቅና ዘለቄታዊውን የልማት ግብ መጀመር ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸና ሐኪሞች ማህበር ያለፉትን እንቅስቃሴዎች የሚዳሰሱበት እና ወደፊት የሚ ደረጉ እንቅስቃሴዎችም ተለይተው የሚወጡበት ነው፡፡ በተመሳሳይም የጤና ጥበቃ ሚኒስር በዘለቄታዊ የልማት ግቦቹ የስነተዋልዶ ጤናን በተመለከተ ከኢሶግ ጋር በጋራ ሊሰሩዋቸው የሚችሉ ጉዳዮችን በሰፊው በውይይት የሚዳሰስ ይሆናል፡፡
ባለፉት 24 አመታት የኢትዮያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር የስነተዋልዶ ጤናን በተለይም የእናቶችን ጤና በተመለከተ የፖሊሲ ንድፈ ሀሳቦችን ከማዘጋጀት ጀምሮ አስፈላጊ የሆኑ ሕግ ጋት እና መሻሻል ያለባቸውን ህጎች እንዲሻሻሉ አስፈላጊውን ድጋፍ አድርጎአል፡፡ ከዚህ በተ ረፈም  በእናቶች ጤና ዙሪያ እና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች የተለያዩ የስራ መመሪያዎችን  አዘጋ ጅቶአል፡፡ በተለይም ከአሁን በፊት በአገር ደረጃ ይሰጡ ያልነበሩ ሕክምናዎችን በአገር ውስጥ እንዲጀመሩ የሚያስችሉ መመሪያዎችን በማዘጋጀት ስራዎቹ እንዲጀመሩ እገዛ አድር ጎአል፡፡
ማህበሩ የተለያዩ አጋሮች ድጋፍ በሚያደርጉባቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች አማካኝነት የተሻለና ጥራቱን የጠበቀ ሕክምና ጋር የተያያዙ የስነተዋልዶ ተግባራት እንዲካሄዱ ጉልሕ ሚና ተጫውቶአል፡፡
የግል የህክምና ዘርፉን አገልግሎት በማሻሻል ረገድም የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር አባላቱን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በተከታታይ ትምህርት እንዲያገኙ እንዲሁም በሳይንሳዊ መድረኮችም እንዲሳተፉና ሁሉም አባላት ተገቢውን የህክምና አገልግሎት ለህብረተሰቡ እንዲሰጡ የሚያስችል አቅም የማጎልበት ስራ ተሰርቶአል፡፡ የሙያ ጥራትን በማስጠበቁ ረገድ በ2015-2020/ድረስ የጤና ጥበቃ ሚኒስር የዘርፉን የወደፊት አቅጣጫ እንዳስቀመጠው የሙያ ጥራትን ማስጠበቅ ቁጥር አንድ አጀንዳ በመሆኑ ማህበሩም ይህንን መሰረት በማድረግ ከአሜሪካን የጽንስና ማህጸን ሕክምና ኮሌጅ ጋር በመተባበር ከሚቀጥለው June/2016  ጀምሮ በሚደረገው እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የስነተዋልዶ ሕክምና ደረጃ በጥራት አኩዋያ አንድ ደረጃ ከፍ የሚያደርግ ስራ ለመስራት በእቅድ ላይነው፡፡” እንደ ዶ/ር ደረጀ ንጉሴ ማብራሪያ፡፡   

Read 1515 times