Saturday, 25 February 2012 13:34

የዊትኒ ልጅ ችግር ላይ ነች

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

የዊትኒ ሂውስተን ብቸኛ ልጅ የሆነችው ቦቢ ክሪስቲና ቀጣይ ህይወቷ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች መወሳሰቡን ዘገባዎች አመለከቱ፡፡ የ18 ዓመቷ ቦቢ ክሪስቲና ከእናቷ ሞት በኋላ ሁለት ጊዜ ከጭንቀት ጋር በተያያዘ ሆስፒታል መግባቷን የዘገበው ሲኤንኤን፤  በአደንዛዥ እፅ ሱስና በፋይናንስ ቀውስ ችግር ውስጥ ሳትገባ አትቀርም ብሏል፡፡ ቦቢ ክሪስቲና የእናቷ ቀብር ላይ ላለመገኘት አመንትታ እንደነበር የገለፀው ኒውዮርክ ታይምስ፤ ወጣቷ ቀብሩ ላይ በድብርት ስሜት ከተገኘች በኋላ ለሰዓታት ያለችበት ጠፍቶ ሁኔታው ቤተሰቧን አስጨንቆ እንደነበር ዘግቧል፡፡  አባቷ ቦቢ ብራውን ካለባት የአእምሮ ጭንቀት እንድታገግም ህክምና ማዕከል መግባት እንዳለባት ተናግሯል፡፡

ቦቢ በእናቷ እና አባቷ ችግሮች ተጠምዳ መኖሯ አሁን ላለባት ቀውስ ዳርጓታል የሚል አስተያየት እየተሰጠ ነው፡፡

የቦቢ ክርስቲና አጠቃላይ ሁኔታ ያሳሰባቸው የዊትኒ ቤተሰቦች፤ በየሚዲያው የሚደረገውን የግል ህይወት ክትትል አማርረዋል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ የዊትኒን ቅርሶች ለጨረታ ለማቅረብ ቤተሰቦቿ እየተንቀሳቀሱ ሲሆን 3 ሰዓት ተኩል የፈጀው የቀብር ስነስርዓቷ ፊልም ለገበያ እንደሚቀርብ ታውቋል፡፡ እንደ ሮይተርስ ዘገባ፤ ቦቢ ክሪስቲና በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ከእናቷ የሙዚቃ አልበሞች ሽያጭ እና ሌሎች ውርሶች እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ገቢ ልታገኝ ትችላለች፡፡

 

 

Read 1006 times Last modified on Saturday, 25 February 2012 13:36