Saturday, 30 April 2016 11:46

የዶ/ር አርቲስት ማሕሙድ አሕመድ 75ኛ ዓመት ልደት ይከበራል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

ልደቱን በማስመልከት የፎቶ ዐውደ ርእይ ማክሰኞ ይከፈታል
  የአንጋፋው ድምፃዊ ዶ/ር አርቲስት ማሕሙድ አሕመድ 75ኛ ዓመት የልደት በዓል፣ የፊታችን ሐሙስ በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት በድምቀት እንደሚከበር የበዓሉ አዘጋጅ የአሻራ ፊልምስ ዳይሬክተርና ፕሮዲዩሰር አቶ ታጠቅ ኃይለ ማሪያም ለአዲስ አድማስ ገለፁ፡፡
75ኛ ዓመቱን በማስመልከት 75 የማሕሙድ ፎቶዎች ለእይታ የሚቀርቡበት የፎቶ ዐውደ ርእይ ከነገ በስቲያ እስጢፋኖስ ፊት ለፊት በሚገኘው ማሪዮት ሆቴል ከቀኑ 9፡00 እንደሚከፈት ታውቋል፡፡ በልደት በዓሉ አከባበር ያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት “ቢግ ባንድ” ታጅበው
የማሕሙድን የተለያዩ ዘፈኖች የሚያቀነቅኑ ድምፃውያን የተመረጡ ሲሆን በዕለቱ ማህሙድ ሁለት ዘፈኖቹን ከተጫወተ በኋላ የተዘጋጀለትን ኬክ እንደሚቆርስ አቶ ታጠቅ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ የፎቶ ዐውደ ርእዩም ለተከታታይ ሰባት ቀናት ለእይታ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ታውቋል፡፡ ማሕሙድም ዛሬ ለዝግጅቱ ከአሜሪካ አዲስ አበባ እንደሚገባ አዘጋጁ ጨምሮ ገልጿል፡፡

Read 1563 times