Saturday, 30 April 2016 11:48

የአብዱ ኪያር “ጥቁር አንበሳ” ኮንሰርት ሃሙስ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(4 votes)

የተወዳጁ ድምፃዊ አብዱ ኪያር “ጥቁር አንበሳ” የተሰኘ ኮንሰርት የፊታችን ሃሙስ በላፍቶ ሞል
ይካሄዳል፡፡ ኤሊ ኤቨንትስ ባዘጋጀው በዚህ ኮንሰርት ላይ አብዱ ኪያር ከአራቱም አልበሞቹ የተውጣጡ ሃያ ያህል ዘፈኖችን በመሀሪ ብራዘርስ ባንድ ታጅቦ እንደሚያቀርብና ሄኖክ መሀሪ አብሮት እንደሚያቀነቅን ተገልጿል፡፡ ወጣት ድምፃውያኑ ያሬድ ጥጉ (የመርካቶ አራዳ) እና የትግሪኛ ዘፈን አቀንቃኙ ዳዊትም ነጋ በዕለቱ ስራቸውን ያቀርባሉ፤ ተብሏል፡፡ የአብዱ ኪያር
ፕሮሞተርና ማናጀር የአቡሸማኔ ኢንተርቴይመንት ባለቤት አቶ ብሥራት ሥዩም፤ ኮንሰርቱ በሴኩሪቲና በሁሉም ነገር የተዋጣለት እንዲሆን ከፍተኛ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡ የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺ የመግቢያ ትኬቶች ዋጋ 350 ብር ሲሆኑ መደበኛው 450
ብር ፣ቪአይፒው 950 ብር መሆኑን የገለፁት አዘጋጆቹ፤ ትኬቶቹ በላፍቶ ሞል፣ በጣይቱ ሆቴል፣ በኤግዚቢሽን ማዕከል በዮዬቱ ሰቨን፣ በየሺጥላ ሞባይል፣ በክለብ ኤችቱኦ እና በማፊሞል በመሸጥ ላይ እንደሆ ተገልጿል።ቢጂአይ ኢትዮጵያ የኮንሰርቱ የክብር ስፖንሰር ነው ተብሏል፡፡

Read 1795 times