ከ4 ዓመት በፊት ሊቨርፑል ሲገባም በክለቡ ታሪክ 50 ጎሎች ፈጥኖ በማስመስገብ ምርጡ አጥቂ ተባለ፡፡
በ2008 እና በ2009 እኤአ በእንግሊዝ ፕሪሚዬርሊግና በዓለም እግር ኳስ ምርጥ ቡድን ውስጥ የማይቀር ተመራጭ ሆነ፡፡ በ2008 የአውሮፓ ዋንጫ በፍፃሜ ጨዋታ ስፔንን ከ42 ዓመት በ ኋላ ለድል ያበቃችውን ብቸኛ ጎል አስገባ፡፡
ከ2009 የውድድር ዘመን በኋላ ግን የቶሬስ ታላቅነት እየተሸረሸረ መጣ፡፡ በሊቨርፑል በሄጅሰን አሰልጣኝነት በ23 ጨዋታዎች 9 ጎል ብቻ አግብቶ በጎል ድርቅ ሲመታ የአንፊልዱ ክለብ ለቼልሲ ተጨዋቹን በእንግሊዝ እግር ኳስ ሪኮርድ ሆኖ በተመዘገበ የ50 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ ለማሰናበት ሳያመነታ ቀረ፡፡
በስታምፎርድ ብሪጅ የመጀመርያውን ጎል ማግባት የቻለው ከ903 ደቂቃዎች በኋላ ነበር፡፡ በዚህ ድክመቱ ቀጥሎ በዓምናው ፕሪሚዬር ሊግ 14 ጨዋታዎች ላይ ብቻ ተሰልፎ በወረደው ዌስትሃም ላይ ብቻ አንድ ጎል አግብቶ የመጀመርያ ውድድር ዘመኑን ጨረሰ፡፡
ዘንድሮም ያው ነው፡፡ በሊጉ ጅማሮ እስከ 5 ሳምንት በተደረጉ ጨዋታዎች ኳስና መረብን ማገናኘት ተስኖት ሰነበተ፡፡
የመጀመርያ ጎሉን ማን ዩናይትድ ላይ ሲያገባ ደግሞ በአውሮፓ ጋዜጦች የፊትና ጀርባ ገፅ ሰፊ ሽፋን የነበረው በጨዋታው ቶሬስ ባዶ ጎል መሳቱን ያተተ ነበር፡፡
ከዚያ በኋላ በ25 ጨዋታዎች ጎል ያገባው 2 ብቻ ሆነ፡፡ አሁን ጎል ካገባ 20 ጨዋታ ያለፈው ቶሬስ በቼልሲ በቆየባቸው 12 ወራት በሁሉም ውድድሮች ያገባው 5 ብቻ ነው፡፡
ተጨዋቹ አሁንም ሆነ ወደፊት በቼልሲ እቆያለሁ ብሎ ቢናገርም በዚህ የውድድር ዘመን መጨረሻ በኪሳራ ሊሰናበት እንደሚችል መወራት ጀምሯል፡፡ ከሚፈልጉት ክለቦች አንዱ ከሊጉ የወረደው ዌስትሃም ነው፡፡
ፈርናንዶ ጆሴ ቶሬስ ሳንዝ 27 ዓመቱ ነው ከዓመት በፊት ያለው ሃብት 18 ሚሊዮን ፓውንድ ተገምቷል፡፡
ከ2001 2007 በአትሌቲኮ ማድሪድ 214 ጨዋታዎች አድርጎ 82 ጎሎች
ከ2007 2011 በሊቨርፑል 102 ጨዋታዎች አድርጎ 65 ጎሎች
ከ2011 ጀምሮ በቼልሲ 34 ጨዋታዎች 5 ጎሎች