Saturday, 25 February 2012 14:37

እንደልቡ ጽፎ፣ እንደልቡ የኖረ ደራሲ፡፡

Written by  በዕውቀቱ ስዩም
Rate this item
(0 votes)

ስብሃትን እንዴት ትገልፀዋለህ?

እንደልቡ ጽፎ፣ እንደልቡ የኖረ ደራሲ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የአማርኛ ልቦለድ ውስጥ አዳዲስ ቅርፆችን ያስተዋወቀም ደራሲ ነበር፡፡ በኖረበት ዘመን ሁሉ ማበርከት የሚገባውን ሥራ አበርክቷል ብዬ አምናለሁ፡፡ በህይወት በነበረበት ጊዜ ስለእሱ ብዙ ተብሏል፡፡ በዚህ በኩል ዕድለኛ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ከስብሃት ሥራዎች አብዝተህ የምትወድለት የትኛው ሥራውን ነው? የስብሃት የአፃፃፍ ዘዴ ባንተ የሥነጽሑፍ ሥራ ውስጥ ምን ተጽዕኖ አለው?

ተጽእኖ አለው የለውም ለማለት አሁን በዚህች ቅጽበት ለእኔ አስቸጋሪ ነው፡፡ ግን ሁሌም ስብሃት አሪፍ ደራሲ እንደነበር መናገር ይቻላል፡፡ ከሥራዎቹ መካከል “አምስት ስድስት ሰባት” እና “7ኛው መልአክ” የተባሉት ሥራዎቹን አብዝቼ እወድለታለሁ፡፡ ስብሃት በድንገት ታሞ በማረፉ ለዘመዶቹ ለቤተሰቦቹና ለሚወዱት አንባቢዎቹ መጽናናትን እመኛለሁ፡፡ የእሱንም ነፍስ የዘላለም እረፍት ያደርግላት ዘንድ እመኛለሁ፡፡

 

 

Read 2832 times Last modified on Saturday, 25 February 2012 14:40