Saturday, 21 May 2016 16:34

በአማኑኤል ሆስፒታል የሙዚቃ ዝግጅት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

   ዘሌማን ፊልም ፕሮዳክሽን ከአማኑኤል ሆስፒታል ጋር በመተባበር የፊታችን ረቡዕ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በአማኑኤል ሆስፒታል ግቢ ውስጥ ትልቅ የሙዚቃ ዝግጅት ያካሄዳል፡፡በዝግጅቱ ላይ በህሙማኑ የተመረጡ እውቅ ድምፃዊያን የሚያቀነቅኑ ሲሆን፤ ከተመረጡት ውስጥ ክቡር አርቲስት ማህሙድ አህመድ፣ ክቡር ዶክተርአርቲስት አሊ ቢራ፣ ድምፃዊ ፀሐዬ ዮሀንስ፣ ፀጋዬ እሸቱ፣ ሄለን በርሄ፣ ሚኪያስ ቸርነት፣ ሳያት ደምሴ፣ ዳዊት ፅጌና ራሄል ሃይለ ይገኙበታል ተብሏል፡፡ በዕለቱ ከሙዚቃ በተጨማሪ የተለያዩ ገጣሚያንና
ኮሜዲያኖች ዘግጅታቸውን በማቅረብ ህሙማኑንና ጥሪ የተደረገላቸውን እንግዶ የሚያዝናኑ ሲሆን ለህሙማኑም አጋርነታቸውን ይገልፃሉ ተብሏል፡፡ ብሬማን ፊልም ፕሮዳክሽን ከዚህ ቀደም የአዕምሮ ህሙማን ላይ የሚያጠነጥንና ህሙማኑን እንዴት በፍቅር ማከም እንደሚቻል የሚያሳይ “ሀሪየት” ፊልም ሰርቶ በማቅረብ በተመልካቹ ዘንድ ተወዳጅነትን ማትረፉንና ይህንኑ የፊልም ስም ሀሪየት ሪያሊቲ ሾው ወደተሰኘ የቴሌቪዥን ሾው በመቀየር ለህብረተሰቡ ግንዛቤ እየፈጠረ እንደሚገኝ የሀሪየት ፊልም ደራሲና ዳይሬክተር እንዲሁም የብሬማንፊልም ፕሮዳክሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ብርሃኔ ጌታቸው ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡

Read 1122 times