Saturday, 25 June 2016 12:09

“የራስ እዳ” የግጥም መድበል ተመረቀ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

    ከ1991 ዓ.ም አንስቶ በውትድርና ሙያ ውስጥ የሚገኙትና ለሰላም ማስከበር ደቡብ ሱዳን ጁባ የነበሩት የአየር ኃይል አባል መቶ አለቃ ገዛኸኝ ታደሰ፤ 76 ግጥሞች የተካተቱበት “የራስ ዕዳ” የተሰኘ የግጥም መድበል ባለፈው ሳምንት በቢሾፍቱ ቶሚ ኢንተርናሽናል ሆቴል ተመረቀ፡፡ ከ7ኛ ክፍል ጀምሮ ግጥም የመፃፍ ፍላጎት እንዳደረባቸው የሚናገሩት መቶ አለቃ ገዛኸኝ፤ በመድበሉ የተካተቱት ግጥሞች ከውትድርና በፊትና በኋላ የተፃፉ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ የግጥም መድበሉን አርትኦት የሰራው፣ በቅርቡ ህይወቱ ያለፈው አንጋፋው ሃያሲ አብደላ እዝራ ነው፡፡ መቶ አለቃ ገዛኸኝ፤ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት መሪ መዝሙር ደራሲም ናቸው፡፡ በ103 ገፆች የተመጠነው መፅሀፉ፤ በ30 ብር ከ60 ይሸጣል፡፡

Read 1370 times