Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 03 March 2012 15:03

የፖለቲካ ጥግ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ስለ ጦርነት

የሰው ልጅ ትልቁ ጦርነት ከራሱ ጋር የሚገጥመው ትግል ነው፡፡

ቤን ኦክሪ (ናይጀሪያዊ ደራሲ፣

የአጭር ልብወለድ ፀሐፊ እና ገጣሚ)

በእሳተ ጐሞራ ላይ እየደነስን ነው፡፡

ኮምቴ ዲ ሳልቫንዲ

(ፈረንሳዊ መኳንንት - ከፈረንሳይ የጁላይ

አብዮት በፊት የተሰጠ አስተያየት)

ሰው አበቃለት የሚባለው ሲሸነፍ አይደለም፤ ታክቶት ሲያቆም ነው፡፡

ሪቻርድ ኒክሰን

(የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩ)

እንደወትሮው ሁሉ ድል መቶ አባቶች ሲያገኝ ሽንፈት ግን ወላጅ አልባ ነው፡፡

ጋሊአዞ ቺያኖ

(ጣሊያናዊ ፖለቲከኛ)

ለአንድ ህዝብ በጣም አስቸጋሪ ተግባር አለ ከተባለ ሽንፈትን በፀጋ መቀበል ነው፡፡

ካርል ቮን ኦሲትዝኪ

(ጀርመናዊ የሰላም አቀንቃኝና ጋዜጠኛ)

ጭርሱኑ ካለመዋጋት ይልቅ ተዋግቶ መሸነፍ ይሻላል፡፡

አርተር ሁግ ክሎግ

(እንግሊዛዊ ገጣሚ)

ሁልጊዜም ጠላቶችህን ይቅር በላቸው፡፡ ነገር ግን ስማቸውን ፈጽሞ አትርሳ፡፡

ሮበርት ኬኔዲ

(አሜሪካዊ ከፍተኛ ፖለቲከኛ)

ጠላቶቼን ይቅር ማለት የለብኝም፤ ምክንያቱም ሁሉንም ገድያቸዋለሁ፡፡

ራሞን ማርያ ናርቬዝ

(ስፔናዊ ጀኔራልና ፖለቲከኛ -

በመምቻው ሰዓት ጠላቶቹን ይቅር እንዲል

በቄስ ሲጠየቅ የመለሰው)

ማንንም ወታደር ጠይቅ፡፡ ወንድን መግደል ለሴት ክብር መስጠት ነው፡፡

ዣን ጊራውዶክስ

(ፈረንሳዊ ተውኔት ፀሐፊና ደራሲ)

 

 

 

Read 3113 times Last modified on Saturday, 03 March 2012 15:05