ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በሰራቸው ሶስት ፊልሞች በመሪ ተዋናይነት፤ በፕሮድዩሰርነትና በፊልም ድርሰት ፀሃፊነት የተሳተፈው ኮሜድያኑ አዳም ሳንድለር፤ የዓመቱ መጥፎ ፊልሞችና የዓመቱ መጥፎ ተዋናዮች በሚል የውድድር ዘርፍ ለቀረቡ ሽልማቶች ተፎካካሪ አይኖረውም እየተባለ ነው፡፡ “ጃክ ኤንድ ጂል” በተሰኘ ፊልም አዳም ሳንድለር ብቻ ሳይሆን ረዳት ተዋናዮቹ ኒኮላስ ኬጅና አልፓቺኖም በመጥፎ ረዳት ተዋናይነት መታጨታቸው ታውቋል፡፡ ሁለቱ እውቅ ተዋናዮች የኦስካር ተሸላሚ እንደነበሩ ይታወሳል፡፡