Monday, 05 March 2012 13:28

ሳንድለር በራዚ አዋርድ ሪኮርድ ያዘ

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

ለመጥፎ ፊልም ስራዎችና ባለሙያዎቻቸው በሚሰጠው የራዚ አዋርድ ላይ በ11 ዘርፎች ለሽልማት በመታጨት አዳም ሳንድለር ሪከርዱን እንደያዘ ሎስአንጀለስ ታይምስ ዘገበ፡፡ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በሰራቸው ሶስት ፊልሞች በመሪ ተዋናይነት፤ በፕሮድዩሰርነትና በፊልም ድርሰት ፀሃፊነት የተሳተፈው ኮሜድያኑ አዳም ሳንድለር፤ የዓመቱ መጥፎ ፊልሞችና የዓመቱ መጥፎ ተዋናዮች በሚል የውድድር ዘርፍ ለቀረቡ ሽልማቶች ተፎካካሪ አይኖረውም እየተባለ ነው፡፡

“ጃክ ኤንድ ጂል” በተሰኘ ፊልም አዳም ሳንድለር ብቻ ሳይሆን ረዳት ተዋናዮቹ ኒኮላስ ኬጅና አልፓቺኖም በመጥፎ ረዳት ተዋናይነት መታጨታቸው ታውቋል፡፡ ሁለቱ እውቅ ተዋናዮች የኦስካር ተሸላሚ እንደነበሩ ይታወሳል፡፡

 

 

Read 997 times Last modified on Monday, 05 March 2012 13:30