Monday, 25 July 2016 09:35

ሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር ጭንቀት ውስጥ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

ከ16 ዓመት በፊት የተቋቋመውን በልመና፣ በሴተኛ አዳሪነትና በተለያየ ምክንያት ወላጆቻቸውን ያጡ ከ800 በላይ ሴቶችና ህፃናትን የሚረዳው ሙዳይ በጎ አድራጎት ድርጀት በገቢ እጥረት ጭንቀት ውስጥ መግባቱን አስታወቀ፡፡
ማህበሩ ከኬጂ እስከ 8ኛ ክፍል ለሚያስተምርበት ት/ቤት ለተለያዩ ወጭዎች፣ ከ800 በላይ ለሆኑት ተረጂዎች ምግብ፣ ለተረጂዎች የቤት ኪራይ ክፍያ ለ400 ሕፃናት ወላጆች ለቋሚ ህክምና ለአጠቃላይ ግቢውና ለሰራተኞች ደግሞ እንዲሁም ለመሰል ወጪዎች በየወሩ ከ400-450ሺህ ብር እንደሚጠበቅበት የገለጹት የማህበሩ መስራች ወ/ሮ ሙዳይ ምትኩ፣ ከቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርና ከኑሮ ውድነቱ የተነሳ ጫናውን ሊሸከሙ እንዳልቻሉ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
ማህበሩ እስከዛሬም የሚንቀሳቀሰው በግለሰቦችና በአንዳንድ በጎ ፈቃደኛ ድርጅቶች በየወሩ አነስተኛ ገንዘቦችን በመሰብሰብ እንደሆነ ገልፀውና ማህበሩ በየጊዜው ወጪው እየናረ በመምጣቱ ምክንያት እንዳይዘጋና ከ800 በላይ ተረጂዎች እንዳይበታተኑባቸው ስጋት ላይ መውደቃቸውን ተናግረዋል፡፡
‹‹በየቀኑ ከ20-25 ተረጂዎች በማህበሩ ስር እርዳታ ይደረግልን እያሉ በራችንን ያንኳኳሉ›› ያሉት ስራ አስኪያጇ ያሉትንም ለማኖር ጭንቅ ውስጥ መግባታቸውን ገልፀው ከተማ አስተዳደሩ የራሳችን ማዕከል እንዲኖረንና በርካታ ችግረኞችን ተቀብለን እንድንረዳ የቦታ ጥያቄ አቅርበን ተቀብሎናል ያሉት ወ/ሮ ሙዳይ ከተማ አስተዳደሩ ቦታውን በአፋጣኝ ሰጥቶን ህልማችን እውን እንዲሆን እንፈልጋለን ብለዋል፡፡ ማህበሩ በግቢፈው ውስጥ ‹‹ፍሬሽ ኤንድ ግሪን አካዳሚ›› የተሰኘ ት/ቤት ያለው ሲሆን ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ 8ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ያስፈተነ ሲሆን ሁሉም ተማሪዎች በጥሩ ውጤት በማለፋቸው ደስታ እንደተሰማቸው ወ/ሮ ሙዳይ ገልፀዋል ከዚህ ቀደም ለአጠቃላይ ግቢ ኪራይ 90 ሺህ ብር ይከፍሉ እንደነበር የገለፁት ስራ አስኪያጇ በአሁኑ ሰአት ኪራዩ ወደ መቶ ሺኅ ብር ከፍ በማለቱና ተረጂዎች እየጨመሩና ቦታው እየጠበበ መሄዱ ከገቢ እጥረት ጋር ተደማምሮ ጭንቀት ውስጥ እንደከተታቸው ተናግረው ሁሉም የማህበረሰብ ድጋፍ በማድረቅ ከጭንቀት አንዲያወጧቸው ተማፅነዋል፡፡


Read 1125 times