Monday, 05 March 2012 13:46

“ሲኒማ ሴፍ” ነገ ይመረቃል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

በሁለት ወጣት ባለሃብቶች ተቋቁሞ በቅርቡ ሥራ የጀመረው ሲኒማ ሴፍ ነገ እንደሚመረቅ ሲኒማ ቤቱ አስታወቀ፡፡ በፊንፊኔ ዙርያ ልዩ የኦሮሚያ ዞን ቡራዩ ከተማ ቡራዩ ማርያም ፍቅሩ ሕንፃ የሚገኘው ሲኒማ ቤት ሲመረቅ በወጣት ፊልም ሰሪዎች መካከል የአጫጭር ፊልሞች ውድድር ይካሄል፡፡

ምርቃቱን አስመልክቶ ለአዲስ አድማስ ማብራሪያ የሰጠው የሲኒማ ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ታምራት አበበ ሲኒማ ቤቱ ለአካባቢው ሕዝብ የተሻለ የመዝናኛ እድል መክፈቱን ገልፆ ከሦስት ወር በፊት ተከፍቶ ሥራ ሲጀመር ከፊልም ፕሮዲዩሰሮች ጋር ባለመላመድ የተነሳ ችግሮች መኖራቸውንና አሁን ግን ለውጥ መኖሩን ተናግሯል፡፡ 350 ወንበሮች ያሉት ሲኒማ ሴፍ የሚያሳየው የአማርኛና ሌሎች የሀገር ውስጥ ቋንቋዎችን ፊልሞችን ብቻ ነው፡፡

 

Read 1373 times